English    Amharic
Home  News Forum FAQ Contacts
 
If the text is unreadable, please download this following font Nyala

መነሻ ገጽ

 

facebook ገጻችንን ላይክ በማድረግ ዜናዎችንና መረጃዎችን በቀላሉ ያግኙ !

 
 

ታሪካዊ ዳራ 

ፍትሕ ሚኒስቴር አሁን ያለውን ስያሜ ከመያዙ በፊት የተለያዩ መጠሪያዎችን በመያዝ አወቃቀሩም ሆነ አደረጃጀቱ በየጊዜው ለውጦች ሲካሄዱበት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የሚኖረው አደረጃጀት ያለፈባቸውን ሥርዓተ ማህበራትና ቅርፀ መንግስታት አሠራርና ይዘት በሚያንፀባርቅ መልኩ የተደራጀ ሲሆን ይህም በተለይ ከዳኝነት ሥርዓቱ ጋር እስከ ቅርብ ጊዜያት የነበረው ቁርኝት ለዚህ አመላካች ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ስለሆነም ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርነው ሁሉ ይህ ፅሁፍ የፍትሕ ሚኒስቴር ከየት ተነስቶ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደቻለ፣በየወቅቱ ሲከተላቸው  የነበሩ አሠራሮች ምን እንደሆኑ፣እንዲሁም አሁን ያለው አወቃቀርና የደረሰበት ደረጃ  ከዚህ ቀጥሎ ለማየት እንሞክራለን፡፡

ሀ. ፍትሕ ሚኒስቴር እስከ ደርግ ውድቀት

የፍትሕ ሚኒስቴር በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ-መንግስት ሲሆን ጊዜውም ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም ነው፡፡ በወቅቱም 12 የተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የተቋቋሙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የዳኝነት ሚኒስቴር ነበር፡፡ በወቅቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአገር ዳኞች ዋና አለቃ ፣የሚፈርደውን ፍርድ ሁሉ በፍትሐ-ነገስት[1] ቃል በትጋት የሚጠብቅ ፣የሚፈርደውንና ባገር ውስጥ የሚፈረደውን ፍርድ ሁሉ በመዝገብ የሚፅፍ መሆኑን የሚሉት ተግባርና ኃላፊነት የተሰጡት መሆኑን በዝክረ ነገር ገፅ 68 ላይ በግልፅ ሰፍሮ ይገኛል ፡፡

ከዚህ በኋላ በተደረገው ለውጥ ማለትም በ1914 አካባቢ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የዳኝነት ሚኒስቴር መባሉ ቀርቶ የፍርድ ሚኒስቴር በሚል ስያሜ እንዲጠራ የተደረገው ሲሆን በዚህ የፍርድ ሚኒስቴርነት ሥልጣኑ የፍርድ ሥራ አካሄዱን ይመራ እንደነበር የተለያዩ ፅሁፎች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማቋቋሚያ አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው የዳኝነት ሥርዓቱም ሆነ የፍርድ ሁኔታው በእጅጉ በነገስታቱ መልካም ፈቃድ ላይ መሠረቱን የጣለ ነበር [ ... ]


Search  

News & Events 

  በፍትህ ሚኒስቴር ስር የተደራጀው የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት የ2ዐዐ7 ዓ.ም. የዘመን መለወጫ በአልን በማስመልከት ይቅርታ እንዲሰጥ የውሳኔ ሀሳብ ለኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት በማቅረብ ለ995 ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን ገለፀ፡፡
 Arrow 09/13/2014
  መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንጻር የህዝብ ክንፍ አደረጃጀት ጅምር ውጤቶችን እያስገኘ ነው::
 Arrow 08/29/2014
  ወደ ኢትዮጵያ ለመሻገር የሞከሩ አሥር ኤርትራዊያን ተገደሉ
 Arrow 08/27/2014
  የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ከግድያ ሙከራ አመለጡ
 Arrow 08/27/2014
  የድሬዳዋ የኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ አምስት ሠራተኞች በጽኑ እስራት ተቀጡ::
 Arrow 08/27/2014
  የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሎሚና በአዲስ ጉዳይ መጽሔቶች ክስ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
 Arrow 08/27/2014
  በመልካም አስተዳደር ዙሪያ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ፍትህ ለማስፈን ፋይዳው የጎላ ነው ::
 Arrow 08/25/2014
  የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 16ኛ ምድብ ወንጀል ችሎት የፋክት መጽሄት ክስ መዝገብ ለ3ኛ ጊዜ ተመለከተ፡፡ ተከሳሾቹ በፍርድ ቤቱ አልተገኙም ፤ለማግኘት ባደረኩት ጥረት በመኖሪያ ቤትም በድርጅታቸውም ሊገኙ አልቻሉም ሲል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
 Arrow 08/21/2014
  ፍርድ ቤቱ የሎሚ መጽሄት ዋና አዘጋጅ ባለመገኘታቸው ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
 Arrow 08/21/2014
  ድረ ገፅ ተጠቅመው የተለየዩ ፅሁፎችን በማውጣት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በሚል የተከሰሱትና ጦማሪያን እየተባሉ የሚጠሩት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።
 Arrow 08/21/2014
  ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው የሽብር ድርጅት በመቀላቀል አዲስ አበባ ውስጥ አባላት ሲመለምል የተያዘው ተከሳሽ ጉዳዩ እየተጣራ ነው፡፡
 Arrow 08/19/2014
  የፋክት መጽሄት ጉዳይ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጠበት ተከሳሾቹ ለሁለተኛ ጊዜ በፍርድ ቤቱ አልተገኙም፡፡
 Arrow 08/18/2014 

Justice Branch Offices 

Website Vister Count

248985

Home :   Links Sitemap Contacts Feedback Copy Right  © 2014 ::  Ministry of Justice