የፍትህ ሚኒስቴሩ መልዕክት

የክቡር ፍትህ ሚኒስቴሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ መልዕክት:-

ፍትህ ሚኒስቴር የሀገራችን የዴሞክራሲና ፍትህ መሰፈን፣ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲሁም የህዝቡ የላቀ ተጠቃሚነት ያለ ሕግ የበላይነትና የፍትህ ዘርፍ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡

የአገራችን የፍትህ ዘርፍ ታሪክ ስር በሰደዱ አናቂ የሕግና የአሰራር እንዲሁም የአመለካካት ችግሮች የተተበተበ እና የጉልበተኞች ምርኮኛ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በተጀመረው አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ተቋማችን የሕግ እና ፍትህ ሪፎርም በማከናወን እንዲሁም የአሰራር ችግሮችን በማሻሻል፣ ከሰብአዊ መብት አኳያ የሕግ ታራሚዎችን አያያዝ በማስተካከል ተቋማዊ አግልግሎትን ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊና ውጤታማ የሆኑ የፍትህ ተደራሽነትን በማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ መሠረታዊ የለውጥ ተግባራትን አከናውኗል፣በማከናወን ላይም ይገኛል፡፡

ፍትህ ሚኒስቴር በአገራዊ የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስ በሚደረገው ሰፊና ሁለንተናዊ ርብርብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በአዋጅ ቁጥር 943/2008 በተሰጠው ስልጣን የፍትህ እና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማክበርና ማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ ፍትህን በማስፈን፣ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ ሀገራዊ ተልዕኮውን ከመቸውም ጊዜ በላቀ ደረጃ በመወጣት ላይ ነው፡፡

ተቋሙ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማረጋገጥ የህዝብና የመንግስት አመኔታ የተቸረው ተቋም በመሆን የሀገራችንን ሰላም አስተማማኝና ዘላቂ በማድረግ የተጀመረው የልማት፣ የሰላም፣ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲጎለብት ብሎም የፍትህ ሥርዓትን ግልፅነት፣ ነፃነትና ተጠያቂነት አሰራርን በማሻሻል በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በዘላቂነት ለውጡን ለማፋጠን የነቃና የተጠናከረ የህዝብ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ከመቸውም ጊዜ በላይ ያስፈልጋል፡፡ ፍትህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና መሰረት ነው፡፡

ዜና

የሽግግር ፍትሕ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት መጠናቀቁን አስመልክቶ የተሰጠ የዜና መግለጫ

የሽግግር ፍትሕ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት መጠናቀቁን አስመልክቶ የተሰጠ የዜና መግለጫ

ፍትሕ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ 6 ወራት አፈፃፀሙን ገመገመ

ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ 6 ወራት  አፈፃፀሙን የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች በተገኙበት የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም ገምግሟል፡፡  የተቋሙን የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት የስትራቴጂክ…

ኢትዮጲያ እና አሜሪካ ግንኙታቸውን ስለሚያጠናክሩበት ሁኔታ ተወያዩ

ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግስት ህግ እና ፍትህ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ከ JOHN " JT " TOMASZEWSKI (Africa policy Ranking member JiM Risch (R-ID) U.S. Senate Committee on…

የ2015 ስኬቶቻችን

ቅሬታ አፈታት
1,122 ቅሬታ ቀርቦ 1,110 ፈጣን ምላሽ አገኘ
0
የማጥራት ምጣኔ
0
33,910 መዛግብት ላይ ክርክር ተደረገ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ከሰጠባቸዉ 14,182 መዛግብት ዉስጥ በ13,744 (97) ዓቃቤ ህግ ረታ።​
0
በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በቀረቡት 706 መዛግብት ላይ ዉሳኔ ተሰጠ፤ በ814 መዛግብት ላይ ክርክር ተደረገ
0
የህግ ምክር ለመንግስት ተቋማትና ግለሰቦች ተሰጠ።
0
የህግ ምክር ድጋፍ –ያገኙ 994 ሴቶች, 112 ህፃናት, 56 አረጋዉያን, 27 አካል ጉዳተኞች, 5 በደማቸዉ ኤች አይ ቪ ቫይረስ ያለባቸዉ
0
የህግ ረቂቅ ዝግጅት ተከናዉኗል።
0
የፌዴራል ፍርድ ቤት ጠበቆች ፈቃድ ተሰጠ።
0

ራዕይ

በ2022 በአህጉሪቱ ከሚገኙ የፍትህ ተቋማት መካከል በአርአያነት ተጠቃሽ መሆን

ተልዕኮ

የሕዝብ ደኅንነትን ያረጋገጥ ውጤታማ፣ ቀልጣፋና የላቀ አገልግሎት መስጠት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር፣ የሰላም ግንባታን የማስቀጠል እና የኢትዮጵያን መንግሥትና ሕዝብ ጥቅም የሚያስጠብቁ አገልግሎቶችን መስጠት

እሴቶች

የሕግ የበላይነትን ማስከበር እና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት መስጠት