በአዲሱ የመንግስት የተቋማት አደረጃጀት መሰረት የአስተዳደር ስራዎችን እንዲያስተባብርና እንዲመራ የተደራጀው የዋና ስራ አስፈጸሚ ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስትር በመሆን የተደራጀ የስራ ክፍል ነው፡፡ በዚህ የሥራ ክፍል ስር የተደራጁት የስራ ክፍሎች የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት፣ የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት እና የመሰረታዊ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ናቸው፡፡ በመሆኑም የስራ ክፍሉ እና ተጠሪ የስራ ክፍሎች የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖራቸዋል፡፡