ይሕ የሥራ ክፍል በአዲስ መልክ በተደራጀው የመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ውስጥ ተካትቶ እንደራጅ ከተደረጉት ስራ ክፍሎች መካከል አንዱ ሲሆን በስሩ የሕግ ምክር፣ የውል ዝግጅት እና ድርድር ማስተባባሪያ፣ እና የመንግስት ተቋማት ክትትል፣ የክርክርና ፍርድ ማስፈፀም ማስተባባሪያ ይዞ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
- የመንግስትና የሕዝብ ፍትሐብሔራዊ መብትና ጥቅም መከበሩን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
- የመንግስት ተቋማት የሕግ አማካሪዎችና የፍ/ብሄር ጉዳዮች ክትትል ስርዐት መዘርጋት፣
- የመንግስት ተቋማት የሕግ አማካሪዎች ሞያ ብቃት ማረጋገጫና ሰርቲፊኬሽን ስርአት ይቀርፃል፤
- በግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶች የውል ዝግጅት እና ድርድርን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያከናውናል፣ የሕዝብና የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ለማስጠበቅ በሌሎች ጉዳዮች ውል ዝግጅትና ድርድር ያደርጋል ወይም የሚመለከታቸውን አካላት ያማክራል፤
- የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤትን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ ይመሰርታል፤ በከሰሱበት ወይም በተከሰሱበት የፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ ክርክር ያደርጋል፤ በሕግ መሠረት ፍርድን ያስፈፅማል፤
- በተጀመረ ክርክር ተቋማትን ተክቶ በተናጠል ወይም በጋራ ይከራከራል፣ ወይም በክርክር አመራር ላይ ለመሥሪያ ቤቶች አቅጣጫ ይሰጣል፣
- የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸዉ ያልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዩች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ እንዲወሰን ውሳኔ ይሰጣል ወይም የአማራጭ ሙግት መፍቻ ዘዴ አገልግሎት ይሰጣል፣ በውሳኔው መሰረት መፈፀሙን ያረጋግጣል፤
- በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ወክሎ ይከራከራል፤
- የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ ተበዳዩች እንዲካሱ ፣ መልሰው እንዲቋቋሙ እንዲሁም ከጉዳቱ ጋር የተያያዙ የፍትሐብሔር ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ወክሎ የፍትሐብሔር ክስ ያቀርባል ወይም ይደራደራል፤
- መንግስት በዓለምአቀፍ የዳኝነትና ከፊል ዳኝነት አካላት በሚከስበት ወይም በሚከሰስበት ጉዳይ መንግስትን በመወከል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ክርክር ያደርጋል፤ ድርድር ያካሄዳል፤ ውሳኔውንም ያስፈፅማል፤
- የመክስር፣ የዉክልና ጋብቻ እና የጋብቻ ተቃዉሞ፣ ከጋብቻ እድሜ በፊት ለጋብቻ ፍቃድ የመስጠት ስርዐትና አደረጃጀት ይቀርጻል፣ ይተገብራል፣
- በንግድ ድርጅቶች ኪሣራ ወቅት ጣልቃ በመግባት የሕዝብንና የመንግስትን ጥቅም ያስጠብቃል፣
- ከሕግ ውጭ ጋብቻ እንዳይፈፀም ተቃውሞ ያቀርባል፣
- የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤
- ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
- የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
- በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
- ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
- ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
- የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፤
- በስራ ክፍሉ ተልእኮ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
- የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤