የፌደራል ሕጎች ተፈፃሚነት ክትትል ዳይሬክቶሬት

የፌደራል ሕጎች ተፈፃሚነት ክትትል ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ ከዚህ በፊት በነበረው ተልእኮ በተጨማሪ አዲሱ የአስተዳደር ስነስርአት ሕግ ካለው የስራ ጫና አንጻር የመመሪያዎች እርማት፣ ምዝገባና ክትትል ተግባራት በተጨማሪ ለመተግበር በሚያስችል መልኩ የፌደራል ሕጎች ተፈፃሚነት ክትትል ቡድን እና የፌዴራል የአስተዳደር ስነ-ስርአት ሕግ አፈፃጸም ክትትል ቡድን ይዞ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

  1. የፌዴራል ሕጎች ተፈፃሚነት ክትትል እና የተጠያቂነት ስርአት ይቀርፃል፣ ይተገብራል፣ 
  2. የፌዴራል መንግስት ሕጐች ለወጡለት አላማና ወጥ በሆነ መልኩ ተግባራዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤ 
  3. የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች በሕግ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት ተግባርና ኃላፊነት ማከናወናቸውን ያረጋግጣል፤ 
  4. በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የአስተዳደር ስነስርዓት አዋጅ መተግበሩን ይከታተላል፣ 
  5. በአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጁ መሰረት የሚወጡ መመሪያዎችን አስተያየት ይሰጣል፣ ያርማል፣ይመዘግባል፣ ቁጥር ይሰጣል፣ ታትመው መውጣታቸውን ያረጋግጣል፣ ለሚመለከታቸው ሁሉ ተደራሽ ያደርጋል፣ 
  6. በተቋሙ ውስጥ ሕጎች፣ደንቦች እና በተቋሙ የወጡ መመሪያዎችንና የተዘረጉ አሰራሮችን ተጠብቀዉ እየተተገበሩ መሆኑን ያረጋግጣል፣ 
  7. የአስተዳደር ፍትህና የከፊል ዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው መንግስታዊ ተቋማት4 የተሰጣቸው ስልጣን የሕግ የበላይነትና የዜጎች ሕገመንግስታዊ መብቶች ባከበረ መልኩ ስለመተግበሩ ክትትል ያደርጋል፣ 
  8. የአስተዳደር ነክ ፍርድ ቤቶችና ጉባኤዎች አሰራራቸውና የተልእኮ አፈፃጸመቸው የሕግ የበላይነትና የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብቶች ባከበረ መልኩ ስለመተግበሩ ይከታተላል፣ 
  9. ነባር እና አዲስ የሚወጡ የአስተዳደር ሕጎችና የተቋማት ማቋቋሚ አዋጆች የዜጎች በመደበኛ ፍርድ ቤት ፍትሕ የመጠየቅና የመዳኘት መብት የማይጋፉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣ 
  10. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  11. ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  12. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  13. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  14. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
  15. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  16. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  17. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  18. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  19. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  20. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 

Department Lead

ሀወኒ ታደሰ

ዳይሬክተር