የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስትር ሆኖ በስሩ የመረጃ፣ መልእክትና ኩነት ዝግጅት ቡድን እና የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ቡድንን ይዞ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-

 1. የተቋሙ ቃል አቀባይ ሆኖ ይሰራል፣ 
 2. ለሚመለከታቸዉ አካላት የመረጃ መስጫ ስርአት ይዘረጋል፣ ለዜጎች የሚሰጡ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በማደራጀት እና በመተንተን በመረጃ ቋት ውስጥ እንዲከማች ያደርጋል፣ መረጃን ተደራሽ ያደርጋል፣ የመረጃ አዋጁን አፈፃፀም ለሚመለከታቸው አካል ሪፖርት ያደርጋል፣ 
 3. ጋዜጣዊ መግለጫ /Press Release/፣ ጋዜጣዊ ጉባኤ /Press Conference/ እና ቃለ-ምልልስ ያካሂዳል ወይም እንዲካሄዱ ያደርጋል፣ 
 4. በተቋሙ የሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በተመለከተ ዶክመንተሪ ፊልሞች እንዲዘጋጁና እንዲሰራጩ ያደርጋል፣ 
 5. በሚዲያዎችና በተቋሙ መካከል መልካም ግንኙነት እንዲዳብሩ ስልቶችን ይቀይሳል፣ ይተገብራል፣ አፈጻፀሙን ይከታተላል፣ 
 6. ወቅታዊ፣ አለምአቀፋዊና ሃገራዊ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል፣ በመስራያ ቤቱ ተግባራት ላይ የሚኖራቸውን እንድምታ ለበላይ አመራር እና ለሚመለከታቸው አካላት ያሳውቃል፣ 
 7. በተቋሙ ላይ በሚሰነዘሩ ነቀፌታዎች እና ቅሬታዎች ላይ መልስ ይሰጣል ወይም እንዲስጥ ያደርጋል 
 8. የተቋሙን ድረ-ገጽ ያስተዳድራል፣ መረጃ ወቅታዊና ተደራሽ መሆኑን ክትትል ያደርጋል፣ 
 9. የሕዝብ አስተያየትና ግብረመልስ ያሰባስባል፣ ለሚመለከታቸው ያቀርባል፣ 
 10. ቋሚ የኤሌክትሮኒክስና የሕትመት ሚዲያ (የቴሌቪዝን፣ ሬድዮ፣ ጋዜጣ፣ መፅሄትና ማህበራዊ ሚድያ) የተግባቦት እና ገፅታ ግንባታ ማበልፀጊያ ዘዴዎች ይቀርፃል ይተገብራል፣ 
 11. ከመሥሪያ ቤቱ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ፕሮግራም፣ ዕቅዶችና አፈፃፀሞች ጋር ተያያዥነት ያላቸው መልዕክቶችን በመቅረጽ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ያሰራጫል፣ 
 12. የተቋሙ ዋና ዋና ተልዕኮዎች አፈፃፀም ውጤቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ያደርጋል፣ ግብረ መልስ ይከታተላል፣ 
 13. የሚዲያ ዳሰሳ /ሞኒተሪንግ/ ስራዎችን ያከናውናል፣ ለአመራሩ ያቀርባል፣ ውጤታቸውንም ተንትኖ ምላሽ ይሰጣል፣ 
 14. የተጠሪ ተቋማት የመረጃና የሚዲያ ስራዎች ያቀናጃል፣ በመሥሪያ ቤቱ የሥራ ክፍሎች መካከል ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ይዘረጋል፣ 
 15. ሁነቶች ያቅዳል፣ ያስተባብራል፣ መድረኮችን ይመራል፣ 
 16. በሁነቶች ላይ መልዕክቶችን ይቀርፃል፣ በተለያዩ መንገዶች እንዲተላለፉ ያደርጋል፣ ውጤቱን ይገመግማል፣ ሪፖርት ያቀርባል፣ 
 17. ከፍትህ ሚኒስትር ፅ/ቤት ጋር የበላይ አመራሩን የመስክ ጉብኝት ያቅዳል፣ ያስተባብራል፣ ያስፈፅማል፣ 
 18. ከፍትህ ሚኒስትር ፅ/ቤት ጋር የበላይ አመራር መግለጫዎችንና ንግግሮችን ያዘጋጃል፣ 
 19. የመሥሪያ ቤቱን መረጃዎች በፎቶግራፍ፣ በኦዲዮና ቪዲዮ ቀርጾ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ ያዉላል፣ 
 20. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤ 
 21. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
 22. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
 23. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤ የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
 24. ከፍትህ ሚኒስትር ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
 25. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
 26. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
 27. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
 28. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
 29. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤