የንቃተ ህግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት

የንቃተ ህግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ በተቋሙ ያለውን የሰው ሀብት የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት ታሳቢ በማድረግ እና በአሁኑ ወቅት በተለያየ አካላት የሚሰራውን የንቃተ ሕግ፣ የስልጠናና የትምህርት ተግባራት በማቀናጀትና ከዚህ ቀደም የሚገባውን ትኩረት ያልተሰጠው የንቃተ ሕግ ተግባር ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ የተደራጀ ሲሆን በስሩ የንቃተ ሕግ ሰነድ ዝግጅት ቡድን፣ የንቃተ ሕግ ማስፋፊያ ቡድን፣ የዐቃብያነ ሕግ ትምህርትና ስልጠና ቡድን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ትምህርትና ስልጠና ቡድን እና የእውቀት ማበልጸጊያ ማዕከል (ቤተ-መጽሀፍት) በስሩ ይዟል፡፡

  1. የንቃተ ሕግ ማስተማሪያ ሰነዶችን ያዘጋጃል፣ የንቃተ ሕግ መስጫ ዘዴዎችን በመለየት የሕግ ትምህርት ይሰጣል፣የዜጎች ንቃተ ሕግ1 ያሳድጋል፣ 
  2. ለንቃተ ህግ የሚያገለግል ጆርናል ያዘጋጃል፣ ያሳትማል፣ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ያደርጋል፤ 
  3. ቋሚ የገፅ ለገጽ ንቃተ ሕግ ማሳደግያ አደረጃጀቶች ይለያል፣ የንቃተ ሕግ ትምህርት የሚሰጥበት ስርአት ይቀርፃል፣ይተገብራል፣ በአደረጃጀቶቹ የንቃተ ሕግ መሰጠቱን ይከታተላል፣ 
  4. ቋሚ የኤሌክትሮኒክስና ሕትመት ሚዲያ በማቋቋም ወይም የአየር ሰአት በመግዛት/በመከራየት የንቃተ ሕግ ትምህርት ይሰጣል፣ እንዲሰጥ ያደርጋል፣ 
  5. ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ለፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት፣ ሹመኞች፣ ተመራጮች፣ ሰራተኞች እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተሳታፊዎች እንደ የአስፈላጊነቱ የንቃተ ሕግ ይሰጣል፤ 
  6. ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን የሰብአዊ መብት ትምህርት እና የንቃተ ሕግ ለማዳበር በተለያዩ ዘዴዎች ትምህርት ይሰጣል፤ በዘርፉ የተሰማሩ የሚመለከታቸውን አካላት ያስተባብራል፤ 
  7. ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለህብረተሰቡና ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰልጠና ይሰጣል፣ 
  8. ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን የባለሙያዎች አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ አዉደ ጥናቶችና ወርክሾፖች፣የልምድ ልዉዉጥ፣የሥልጠና እና ተመሳሳይ መድረኮችን ያመቻቻል፣ 
  9. የንቃተ ሕግ ተደራሽነትና ያመጣውን ፋይዳ ያጠናል፣ የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፣ 
  10. የተቋሙን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ከአገርቱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ጋር በማጣጣም ይቀርፃል፣ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፣ 
  11. እንደ የስራ ባህሪያቸው የዐቃቢያነ ሕግ እና የአስተዳደር ሰራተኞች የስልጠና ዝርዝር የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ይፈፅማል፣ያስፈፅማል፣ 
  12. የዐቃቢያነ ሕግና የአስተዳደር ሰራተኞች የትምህርትና የስልጠና መመሪያና ማኑዋል ይቀርጻል፣ ያጸድቃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ 
  13. የትምህርትና ስልጠና ፍላጎት የዳሰሣ ጥናት በማካሄድ የአጭርና ረጅም ጊዜ የትምህርትና የስልጠና ፕሮግራሞችን ይቀርፃል፣የስልጠና አሰጣጥ መንገዶችን ይወስናል፣ 
  14. የማሰልጠኛ ማተሪያሎች ያዘጋጃል፣የተዘጋጁትን ይዘታቸው ይገመግማል፣በውድድር የሚዘጋጅ የማሰልጠኛ ርዕስ ጉዳይ አማራጮችን በመለየት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ 
  15. የክህሎት ክፍተት ዳሰሳ ያካሄዳል፣ የስልጠና ፕሮግራሞች ይቀርፃል፣ሰልጣኞችና አሰልጠኞች የሚመለመሉበት መስፈርት ያወጣል፣የስልጠና ዘዴዎችን በመለየት ስልጠና ይሰጣል፣ 
  16. ሰፊና ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ስልጠና ፍላጎት በመለየት በሕግና ፍትሕ ምርምርና ስልጠና ኢንስትትዩት እና በሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፣ 
  17. ልዩ ክህሎት የሚጠይቁ የስልጠና መስኮችን በመለየት ዐቃቢያን ሕግ የረጅምና የአጭር ጊዜ የቅድመና የስራ ላይ ስልጠና እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡ 
  18. የተቋሙን የዕውቀት ማዕከል (ቤተ-መጽሀፍት) ያደራጃል፣ የቤተ-መጽሀፍት አገልግሎት ይሰጣል፣ ያስተዳድራል፣ 
  19. የሰው ሃብት አቅም ግንባታ ሥራን ለመተግበር በየጊዜው የሚወጡትን መመሪያዎችን ለማስተዋወቅ ሴሚናሮች ወርክሾፖች እና ሲፖዚየሞች ያዘጋጃል ፣ ያስተባብራል፣ 
  20. ከተለያዩ ማስልጠኛና የትምህርት ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ትምህርትና የስልጠና ዕድሎችን ያፈላልጋል፣ በተገኙ የአጫጭርና የረዥም ጊዜያት ስልጠናዎች ሰራተኞች ተጠቃሚ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣በዕጩዎች የሚሞሉ የግዴታ ውል ቅጾችን ያጸድቃል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ 
  21. አዲስ ለሚቀጠሩ ሰራተኞች ተግባር ተኮርና የቅድመ ስራ ስልጠና እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡ 
  22. ለትምህትና ስልጠና የሚመለመሉ ሰራተኞች በመስፈርቱ መሰረት መመልመላቸውን ይገመግማል፣ 
  23. ስልጠና ሂደትና ያስገኘው ውጤት ይገመግማል፣ግብረመልስ ይሰጣል፣በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ጉዳዮች ለይቶ ፣ ያሻሽላል፣ 
  24. የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ውጤታማነትና ተጽእኖ (Impact) ግምገማ ጥናት ያካሄዳል፣የስልጠና ምዘና እና ማረጋገጫ ስርዓት ይዘረጋል፣ 
  25. የውስጥ አሰልጣኞችን ይመለምላል፣ አቅማቸውን ይገነባል፣ በውስጥ አቅም ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፣ የዉስጥና የዉጪ አሰልጣኞች መረጃ ቋት ያደራጃል፣ 
  26. የስልጠና መረጃዎችን ይይዛል፣ የሰልጣኞች ፕሮፋይል ያደራጃል 
  27. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  28. ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  29. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  30. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  31. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 
  32. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
  33. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  34. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  35. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  36. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  37. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 

Department Lead

እንዳልካቸው ወርቁ ለሜቻ

ዳይሬክተር

Department Info

+251112345678
Head Quarter, 2nd Floor, 208