የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለሚኒስትር ሆኖ የሚከተሉት ተግባር እና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡- 

  1. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤
  2. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  3. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
  4. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
  5. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  6. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
  7. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
  8. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
  9. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
  10. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤
  11. የተቋሙን ስትራቴጂክና ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ የዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ ስርዓት ይዘረጋል፣ስትራተጅያዊ እይታ አማላካች ግቦችና ቀርፆ እንዲተገበር ያደርጋል፣የአፈጻጸም መመዘኛ መስፈርቶችን በማዘጋጀት በሥራ ላይ ያውላል፣
  12. የእቅድ በተቀመጠለት ጊዜና በጀት መሠረት እየተፈጸመ መሆኑን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
  13. የተቋሙን ዕቅድና ሪፖርት ያዘጋጃል፣ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ላይ ለስራ ክፍሎች ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  14. ለተለያዩ የሥራ ክፍሎች በእቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት ወቅት አስፈላጊውን ሙያዊ እገዛና ድጋፍ ያደርጋል፣
  15. የተጠሪ ተቋማትን እቅድ እና ሪፖርት የቀናጃል፣
  16. የተቋሙን ፕሮግራም በጀት ያዘጋጃል፣ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
  17. ከፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን አመታዊና ወርሃዊ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  18. የየሩብ ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈፃፀም ሪፖርት ያደራጃል፣ ይገመግማል ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፣
  19. ለዘርፎች የተመደበዉን የበጀት ያሳዉቃል፣በየወሩ አጠቃቀማቸዉን እየተከታተለ አስፈላጊዉን ማስተካከያ እንዲያደረጉ ያደርጋል፣
  20. የበጀት እጥረት ሲያጋጥም ተጨማሪ በጀት እና የበጀት ዝውውር ጥያቄዎች ተቀብሎና አጣርቶ እንዲፈቀድ የውሳኔ ሃሳብ ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፣ ሲፈቀድ ስራ ላይ እንዲዉል ክትትል ያደርጋል፣ 
  21. የፕሮጀክት ሰነዶች ከተቋሙ ስትራቴጅክ እቅድና የስራ ባህሪይ መሠረት የተዘጋጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
  22. የፕሮጀክቶች ዝግጅትና አፈጻጸም ክትትል ሥራዎች እና የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ችግሮች የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ይለያል፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን ያመነጫል፣ ለሚመለከተው ያቀርባል ሲወሰንም አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 
  23. የፕሮጀክት አፈፃፀም ክንውን ሪፖርት ወቅቱን ጠብቆ መቅረቡን ያረጋግጣል፤ ይገመግማል፤ የተጠቃለለ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
  24. ለተቋሙ ኘሮጀክቶች ዝግጅትና ክትትል የሚረዱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚረዱ ቅጾችን ቀርጾ ተግባራዊ ያደርጋል ፣
  25. በተጨማሪም ከሚኒስትር የሚሰጡ ተግበራትን ያከናውናል፤

Department Lead

ደሳለኝ መንግስቴ ምህረቱ

ዳይሬክተር