የወንጀል ተጎጂዎች፣ ጠቋሚዎች እና ምስክሮች ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ተግባር እና ኃላፊነት

ይህ ዳይሬክቶሬት በባህርዩ ከወንጀል ጉዳዮች ክትትል ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው በመሆኑ፣ በዚህ ዘርፍ ስር የታዩ የወንጀል ጉዳዮች ላይ ጥቆማ የሚሰጡ እና ምስክሮች ለጥቃት ተጋላጭ በመሆናቸው ለምስክሮች እና ጠቃሚዎች የሚደረገውን ጥበቃ በጥብቅ ቅንጅት በመፈጸም ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ ካሉት ዳይሬክቶሬቶች ጋር ያለውን የጎንዮሽ ትስስር ታሳቢ በማድረግ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የሚከተሉት  ተግባር እና ኃላፊነት ይኖሩታል፡- 

ይህ የስራ ክፍል የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ቡድን እና የወንጀል ተጎጂዎች አገልግሎት ቡድንን ይዞ የሚከተሉት ተግባር እና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡ 

 1. የሚቀርቡ የጥበቃ ተጠቃሚነት ማመልከቻዎችን በመቀበል አጣርቶ ዉሳኔ ይሰጣል፣ 
 2. የጥበቃ እርምጃ አይነት ለመወሰን ግምት ዉስጥ መግባት ያለባቸዉን ጉዳዮችን ያጣራል፣ 
 3. የጥበቃ ስምምነት ዉል ያዘጋጃል፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በማፀደቅ ከጥበቃ ተጠቃሚ ጋር ይፈራረማል፣ ጥበቃዉን ይሰጣል፣ 
 4. አካለ መጠን ካላደረሱ ሰዎች ጋር ልዩ የጥበቃ ዉል ይፈፅል፣ የተገባዉን የጥበቃ ስምምነት ፍ/ቤት አቅርቦ ያጸድቃል፣ 
 5. የጥበቃ እርምጃዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከሚያግዙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን ይለያል፣ በቅንጅት ይሰራል፣ 
 6. ለጥበቃ ተጠቃሚዎች የሕግና ስነልቦና ምክርና ድጋፍ አገልግሎት ይሰጣል ወይም እንዲያገኙ ያደርጋል፣ 
 7. በወንጀል ምስክር ወይም ጠቋሚ ላይ የበቀል እርምጃ ወስዷል የተባለ አካል ወይም ሰዉ ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጣራበት ትእዛዝ ይሰጣል፣ የተመሩ ጉዳዮችንም ይከታተላል፡፡ 
 8. ጥበቃ በተሰጣቸዉ ሰዎች ላይ በየጊዜዉ ስለሚኖር የኑሮ እና የስጋት ሁኔታ ይከታተላል፤ 
 9. ጉዳት ለደረሰባቸው ለወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች በሕግ መስረት እስፈላጊውን አገልግሎት እና ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፣ 
 10. የገንዘብ አቅም ለሌላቸዉ እንዲሁም ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የወንጀል ተጎጂዎች ለደረሰባቸው ጉዳት በፍትሐብሔር ካሳ እንዲያገኙ ክትትል ያደርጋል፣ 
 11. ከሚመለከተዉ የፖሊስ ተቋም ጋር በመተባበር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ አደጋና ጥቃት እንዳይደርስባቸዉ የአካልና የንብረት ጥበቃ እንዲያገኙ ያደርጋል፣ 
 12. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
 13. ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
 14. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
 15. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
 16. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
 17. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
 18. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
 19. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
 20. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
 21. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የባለድርሻ አካላት ክፍሎች የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
 22. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 

Department Lead

ፍርዴ ቸሩ መለሰ

ዳይሬክተር