የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀነራል

የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ ከዚህ በፊት የነበረው ንቃተ-ሕግ ትምህርትና ስልጠና ተግባራት ጫና በመቀነስ የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ተደራሽነት ተግባራት ጥራት ባለው መልኩ ለማከናወን በሚያስችል አግባብ ተደራጅቷል፡፡ በስሩም የሕግ ጥናት፣ ረቂቅ ሕግ ዝግጅት እና ማረም ቡድን፣ የህጎች ማጠቃለልና ስርጭት ቡድን፣ የወንጀል ፍትህ ፖሊሲና የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ማስተግበሪያ ቡድን የያዘ ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

 1. የሕግ ጥናትና ረቂቅ ዝግጅት ጥራት ማረጋገጫ መስፈርት ይቀርፃል፣ ይተገብራል፣
 2. አዲስ ሕግ የሚወጣላቸውና የሚሻሻሉ ሕጎች የትንበያ ጥናት ያካሂዳል፣የረቂቅ ሕግ ዕቅድ በማውጣት ይተገብራል፣
 3. በፌዴራል መንግሥት የሚወጡ ሕጎች ጥናት ያከሂዳል፣ የሕግ ረቂቅ ያዘጋጃል፣ ያርማል፣
 4. ከክልሎች ጥያቄ ሲቀርብለት የሕግ ረቂቅ ያዘጋጃል፣ በተዘጋጁት ረቂቆች አስተያየት ይሰጣል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሞዴል ረቂቅ ሕጎች ያዘጋጃል፣
 5. አስፈፃሚ የመንግስት አካላት ሕግ የማመንጨትና የማርቀቅ ብቃት እንዲኖራቸው ድጋፍ ይሰጣል፣
 6. የውል አስተዳደርና አፈፃጸም የሕግ ማዕቀፍ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ያለው አመቺነት ያጠናል፣ የማሻሻያ ረቂቅ ሕግ ያዘጋጃል፣
 7. አዲስ የሚረቀቁና የሚሻሻሉ ሕጎች ለንግድና ኢንቨስትመነት መስፋፋትና ሕጋዊ ውድድር የሚያበረታቱና ሕገወጥነትን የሚከላከሉ መሆናቸው ያረጋግጣል፣
 8. የወጡ ሕጎችን መታተማቸው ይከታተላል፣ በተለያዩ ዘዴዎች ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፣
 9. የወጡ ሕጎች በማሰባሰብና በማጠቃለል ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፣
 10. በኮድ ደረጃ መጠቃለል ያለባቸው ሕጎች በመለየት አዘጋጅቶ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፣
 11. የወጡ ሕጎች ያመጡት ፋይዳ በማጥናት የማሻሻያ ምክረ ኃሳብ ያቀርባል፣
 12. በወንጀል ፍትህ ፖሊሲ ሕግና አሰራር ሊወጣላቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ይለያል፣ ረቂቅ ያዘጋጃል፣ በሚመለከታቸው አካላት ሲፀድቅ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፡፡
 13. የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ይቀርፃል፣ለአተገባበሩ መውጣት ያለባቸው ሕጎች፣አሰራሮችና ፕሮግራሞች ረቅቅ ያዘጋጃል፣ በሚመለከታቸው አካላት ሲፀድቅ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ፈፃሚ አካላትን ያስተባብራል፣የክትትል ድጋፍ አሰራር ስርአት ይቀርፃል ፣ይተገብራል፣
 14. የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ፈፃሚ አካላት አቅም ግንባታ ተግባራት እንዲከናወን ያደርጋል፣
 15. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
 16. ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
 17. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
 18. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
 19. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
 20. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
 21. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
 22. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
 23. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
 24. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
 25. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤

Department Lead

አዲስ ጌትነት ተመስገን

ዳይሬክተር ጀነራል