የሕግ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ተግባር እና ኃላፊነት

የሕግ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስትር ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡- 

  1. የምርመራ፣ የክስና ክርክር መዝገቦች ቆጠራ (Case Inventory) ጥናት ውጤት ትክክለኝነት ያረጋግጣል፣ 
  2. የወንጀል መዝገቦችና ተጠርጣሪዎች/ተከሳሾች ብዛት፣ ስም ዝርዝራቸው፣ የቆይታ ጊዜያቸውና የቆዩበት ምክንያት እና በአጠቃላይ የቅልጥፍና ደረጃውን እንዲሁም ለተፋጠነ ፍትሕ ዕንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ያጠናል፣ የማሻሻያ ሐሳብ ያቀርባል፣ 
  3. ምርመራቸው ያለቀና በክስ እና ክርክር ሂደት ያሉ መዝገቦች በታቀደ ወይም ድንገተኛ የሕግ ኦዲት በማካሄድ የጥራት ደረጃዉን ከሕግና ከማስረጃ አንፃር ያጠናል፣ የማሻሻያ ሐሳብ ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  4. ከሕግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ግኝት በመነሳት አግባብነት ያላቸው መሻሻያዎች እንዲደረጉ ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የማሻሻያ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮችን በየደረጃው ላሉ ኃላፊዎች ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  5. የህግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ግኝቱን ለአሰራር ማሻሻያና ለዐቅም ግንባታ ተግባራት እንዲውሉ ለሚመለከተዉ አካል ያስተላልፋል፣ 
  6. የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 42(1)(ሀ) እና በተለያዩ መንገድ የተቋረጡ ሁሉም መዝገቦች ግልባጭ ለስራ ክፍሉ መድረሱን ያረጋግጣል፣ የውሳኔዎቹ ሕጋዊነት እና አግባብነት ይመረምራል፣ ተገቢው ማስተካከያ እንዲደረግ ያደርጋል፣ 
  7. በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሪ ትዕዛዝ የሚጠየቅባቸው ጉዳዮች የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል፣ 
  8. የዐቃብያነ ሕግ ፍቅደ ስልጣን አጠቃቀም ጉድለት ያለባቸዉን ጉዳዮች በመለየት የውሳኔ ወጥነት ለማረጋገጥ መመሪያ እንዲወጣ ያደርጋል፣ 
  9. ለትርጉም የተጋለጡ ህጎችንና የሕግ አንቀፆችን በጥናት መለየትና ተገማች ዉሳኔ ለመስጠት የሚረዳ ጋይድ ላይን እንዲቀረጽ ሀሳብ ያቀርባል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ 
  10. ከክስና ምርመራ ጋር የተያያዙ የአሰራር ስርዓቶች እንደዘረጋ ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣ ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፣ 
  11. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  12. ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  13. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  14. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  15. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
  16. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  17. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  18. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  19. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  20. በስራ ክፍሉ ተልእኮ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  21. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤

Department Lead

ልዑል ካህሳይ ወልዱ

ዳይሬክተር