የይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ጽ/ቤት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የተደራጅ የስራ ክፍል ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ሃለፊነት ይኖሩታል፡-
- ከሕግ ታራሚዎች እና ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሚቀርቡ የይቅርታ ጥያቄን በመመርመር ለይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ያቀርባል፣
- የቦርድ ውሣኔ ሃሣብና ይቅርታ የሚገባቸዉን ታራሚዎችን ዝርዝር መግለጫ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀርባል፣
- የይቅርታ ዉሳኔዎችን ለታራሚዎች እና ለማረሚያ ቤት ያሳውቃል፣ በውሳኔ መሰረት መፈፀሙን ይከታተላል፣
- ከክልሎች የቀረቡ ፌዴራል ጉዳይ ታራሚዎች የክልል የቦርድ የዉሳኔ ሀሳብ ለፌደራል ይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ያቀርባል፣ በውክልና በተሰጡ ጉዳዮች ይቅርታ አሰጣጥ ክትትል ያደርጋል፣
- በተጭበረበረ ማስረጃዎች በይቅርታ የወጡ ታራሚዎች ጉዳይ መርምሮ ለቦርድ የውሣኔ ሐሳብ ያቀርባል፣
- የፌዴራልና የክሎች የይቅርታ አሰጣጥ ተቀራራቢ እና ተናባቢ እንዲሆን ለክልሎች የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጋራ መድረክ ያቀርባል ፣
- በይቅርታ አሠጣጥ ዙሪያ የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎች ያጣራል፣ በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲሰጣቸው የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል፣
- ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመመካከር የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
- የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤
- ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
- የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
- በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
- ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
- ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
- የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
- በስራ ክፍሉ ተልእኮ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
- የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤