የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት

የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስትር ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-

 1. ከመንግስትና ከለጋሽ ድርጅቶች የሚገኝ ገንዘብ እና ሐብትና ንብረት በሕግ መሠረት ስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣ 
 2. የውስጥ ኦዲት ደረጃን በጠበቁ መልኩ የኦዲት ሪፖርቶች ያዘጋጃል፣ 
 3. የኦዲት ግኝቶች ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀርባል፣ በግኝቶች መሠረት የተወሰዱ እርምጃዎችን የሚያሳይ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ 
 4. የተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶችን በመገምገምና ስጋት ያለባቸውን በመለየት ተገቢ ትኩረት ተሰጥቷቸው የተሻለ የአሰራር ሥርዓት እንዲሰፍን ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊዎችና ለተመርማሪ የስራ ክፍሎች የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣ 
 5. ዘመናዊ የኦዲት ዘዴዎችና ቴክኒኮችን በማጥናት የኦዲት ሥራ የሚሻሻልበት፣ የሚቀላጠፍበትንና የተሻለ ውጤት የሚያስገኝበትን አሰራር ይቀርጻል፣ ይተገብራል፣ 
 6. በየጊዜው በሚወጣው የኦዲት መመሪያ ከተግባር ጋር በማገናዘብ አስፈላጊ የሆኑ የማሻሻያዎችን ያደርጋል፣ 
 7. የፋይናንስ ጥናት እና የሱፐርቪዢን ሥራ ያከናዉናል፤ ክትትል እና ግምገማ ያደርጋል፤ 
 8. የኦዲት መረጃዎችን እና የተዘጋ ሂሳብ ማመዛዘኛ ሪፖርቶችን በመሰብሰብ ኦዲት በማድረግ ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፣ 
 9. የኦዲት ግኝቶች ማስተካከያ መደረጉን ይከታተላል፣ 
 10. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
 11. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
 12. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
 13. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
 14. ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
 15. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
 16. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
 17. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
 18. በስራ ክፍሉ ተልእኮ ባለድርሻ አካለት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
 19. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 
 20. በተጨማሪም ከጠቅላየ ዐቃቤ ህግ የሚሰጡ ተግበራትን ያከናውናል፤