በሕግ ጉዳዮች የአለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች አፈፃፀም ክትትል እና በሕግ ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብር የሚመለከቱ ተግባርና ኃላፊነት ሳይነጣጠሉ በአንድ ማዕከል በተደራጀ መልኩ ለመተግባርና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዘርፉ ያለውን ማዕከላዊ ባለስልጣንነቱን ለማጠናከር በስሩ የዓለም አቀፍ ስምምነቶች አፈጻፀም ክትትልና ሪፖርት ዝግጅት ቡድን እና በሕግ ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብር ቡድን በመያዝ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
- ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውን ወይም የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ፣አህጉራዊ የሁለትዮሽ ስምምነቶች አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ሪፖርትና ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስርዐት ይዘረጋል፣ ብሔራዊ የአፈፃፀም ወቅታዊ ሀገራዊ ሪፖርት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አዘጋጅቶ ያቀርባል፤
- የሁለትዮሽ፣ ክፍለ አህጉራዊና አህጉራዊ ግንኙነቶች ግዴታዎችን ለመወጣት ተሣትፎና ክትትል ያደርጋል፤
- ዐለም አቀፍና አህጉራዊ መንግስታዊና መንግስታዊ ያለሆኑ ተቋማት በመንግስት ላይ ለሚያቀርቡት ክሶች፣ አቤቱታዎች ሕግ ወይም ፍትሕ ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፣
- ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከት ከሀገር ውስጥ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፤
- በሕግና ፍትህ ጉዳዮች ከዲያስፖራ ማህብረሰብ ለሚቀርቡ ሕግ ነክ ጥያቄዎች እና አቤቱታዎች ምላሽና ድጋፍ ይሰጣል፣
- በሕግና ፍትህ ጉዳዮች ትኩረት የሚደረግባቸዉ መስኮች፣ ትብብር የሚደረግባቸዉ ሀገራትና አለም አቀፍ ተቋማት መለየት የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ያዘጋጃል፣ ይተገብራል፣
- በሕግና ፍትህ ጉዳዮች አለም አቀፍ ትብብር የሚያሳልጡ ማስፈፀሚያ ስልትና ስርአት በመቅረጽ ይተገብራል፣
- በሕግና ፍትህ ጉዳዮች አለም አቀፍ ትብብር የተደረጉት ስምምነቶች ያመጡት ፋይዳ በማጥናትና የማሻሻያ ሐሳብ ያቀርባል፣
- በሕግና ፍትህ ጉዳዮች አለም አቀፍ ትብብር የማዕከላዊ ባለስልጣንነትን አቋም ማጠናከርና የሁለትዮሽና አለምአቀፍ ስምምነቶች የግንኙነት መስመሩ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚያልፉበት ስርዐት ይቀርፃል፣ ይተገብራል፣
- በሕግና ፍትህ ጉዳዮች አለም አቀፍ ትብብር የመረጃ ማዕከል ያቋቁማል፣ የመረጃ ልዉዉጥ ስርዐቱን ያደራጃል፣መረጃው ለሚመለከታቸው ያዳርሳል፣
- በአለም አቀፍ፣አህጉራዊ፣የሁለትዮሽ ስምምነትና በእንካ ለእካ (Reciprosity) መርህ መሰረት ይሰራል፣
- የአሳልፎ መስጠት ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በመቀበል ለሌሎች ሀገራት ያቀርባል፤ አፈጻፀማቸውን ይከታተላል፤ ከሌሎች ሀገራት የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በመቀበል ምላሽ ይሰጣል፤
- በወንጀል ጉዳዮች የፍትህ ትብብር ረቂቅ ስምምነቶችን ያዘጋጃል፣ ከሌሎቸ ሀገሮች በሚላኩ ረቂቅ ስምምነቶች ላይ አስተያየት ይሰጣል፤ ሲፈቀድ ድርድር እና ስምምነቶችን ያደርጋል፤
- በወንጀል ጉዳዮች የፍትህ ትብብር ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በመቀበል ለሌሎች ሀገራት ያቀርባል፤ አፈጻፀማቸውን ይከታተላል፤ ከሌሎች ሀገራት የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በመቀበል ምላሽ ይሰጣል፤
- በፍትሐብሔር ጉዳዮች የፍትሕ ትብብር ረቂቅ ስምምነቶችን ያዘጋጃል፣ ከሌሎቸ ሀገሮች በሚላኩ ረቂቅ ስምምነቶች ላይ አስተያየት ይሰጣል፤ ሲፈቀድ ድርድር እና ስምምነቶችን ያደርጋል፤
- በፍትሐብሔር ጉዳዮች የፍትሕ ትብብር ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በመቀበል ለሌሎች ሀገራት ያቀርባል፤ አፈጻፀማቸውን ይከታተላል፤ ከሌሎች ሀገራት የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በመቀበል ምላሽ ይሰጣል፤
- ፍርደኞችን የማስተላለፍ ረቂቅ ስምምነቶችን ያዘጋጃል፣ ከሌሎቸ ሀገሮች በሚላኩ ረቂቅ ስምምነቶች ላይ አስተያየት ይሰጣል፤ ሲፈቀድ ድርድር እና ስምምነቶችን ያደርጋል፤
- ፍርደኞችን የማስተላለፍ ጥያቄዎችን በመቀበል ለሌሎች ሀገራት ያቀርባል፤ አፈጻፀማቸውን ይከታተላል፤ ከሌሎች ሀገራት የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በመቀበል ምላሽ ይሰጣል፤
- በሀገር ውስጥ የተሰጡ የፍርድ ቤት ትእዛዞችና ውሳኔዎች በውጭ መንግስት ወይም በአለም አቀፍ ድርጅት መፈጸማቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል እንዲሁም በውጭ መንግሰት ወይም አለም አቀፍ ድርጅት የተሰጡ ውሳኔዎች በሀገር ውስጥ በሕግ መሰረት ያስፈጽማል፣
- በውጭ አገር የሚካሄዱ ስብሰባዎች፣ ወርክሾችና ስልጠናዎች ተሳትፎ ያስተባብራል፣ የጉዞ ሪፖርት በማቀናጀት፣ ልምድ ይቀምራል፣ እንዲሰፋ ያደርጋል፣
- የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
- ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
- የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
- በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
- ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
- ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
- የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
- በስራ ክፍሉ ተልእኮ በለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
- የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤