የሚኒስትር ጽ/ቤት ቀደም ሲል የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በሚል የተደራጀ ሲሆን በስሩ የህግ አማካሪዎች እና የቅሬታ አጣሪ ቡድን፣ የተጠሪ የስራ ክፍሎች እና ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ቡድን እንዲሁም የሥነ ምግባር ክትትል ቡድንን በስሩ ይዞ የሚከተሉት ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡
- ፍትህ ሚኒስትሩን ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ያማክራል፤ አማካሪዎችንና የአስተዳደር ሰራተኞችን ያስተባብራል፣ ያሰማራል፣ የስራ አፈፃፀማቸውን ይገመግማል፣ ይመዝናል፤
- ፍትህ ሚኒስትሩ በመደበኛ ስብሰባና ከመ/ቤቱ ውጭ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በማይገኝበት ጊዜ ወክሎ ይሳተፋል፣ ለተለያዩ ስብሰባዎች እና ፕሮግራሞች የሚቀርቡ ንግግሮችን ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤
- የበላይ አመራሩ ለሚሳተፉባቸው ብሔራዊና አለም አቀፍ ስብሰባዎች አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች እና መግለጫዎች ተሟልተው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤
- ለፍትህ ሚኒስትሩ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ ይሰጣል ፣ በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች የውሳኔ ሓሳብ ያቀርባል፣
- የማኔጅመንት ስብሰባዎችን ያቀናጃል፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመመካካር አጀንዳ ይቀርፃል፣ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ በአግባቡ መያዙን ያረጋግጣል፣ የተሰጡ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫዎችን ተፈጻሚነት ይከታተላል፤
- የፍትህ ሚኒሰቴር እና የክልል ፍትህ ቢሮ የጋራ መድረክ ፀሐፊ ሆኖ ያገለግላል፣ ያስተባብራል፣ ከፍትህ ሚኒስትሩ በሚሰጠው አቅጣጫ አጀንዳ ይቀርፃል፣
- ከሥነ-ምግባር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን በመቀበል እንዲጣራ ለሚመለከተው አካል ይመራል፣ ተጣርቶ ሲቀርብም መርምሮ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ውሳኔ ያቀርባል፣
- ለበላይ አካላትና ለተለያዩ መ/ቤቶች የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ይከታተላል፣ ግብረመልስ ይሰጣል፣
- ለተቋሙ ተልዕኮ ማሳካት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ይለያል፣ መፍትሔ እንዲያገኙ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፤
- በመ/ቤቱና በሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚደረጉ የቅንጅት ስራዎች ያስተባብራል ፣የመግባቢያና የፕሮቶኮል ስምምነት ሰነዶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ያስፈጽማል፣
- በፍትህ ሚኒስትሩ ሰብሳቢነት የሚመሩ ቦርዶችን፣ ግብረኃይሎችን እና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን ይከታተላል፤ ይደግፋል፣
- ከተለያየ አካላት የሚቀርቡ አስተያየቶችን ምርምሮ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተጠቃለለ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል ፣ የተሰጡ ውሳኔዎች አፈፃፀም ይከታተላል፣
- የተጠሪ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርና ቋሚ የክትትልና ድጋፍ ስርአት ይዘረጋል፣
- በተጠሪ ተቋማት የሚወጡ ህጎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ፕሮግራሞችንና ዕቅዶችን ይከታተላል፣
- ለፍትህ ሚኒስትር ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎችን ያቀናጃል፣ ያስተባብራል፣ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ላይ ግብረ መልስ ይሰጣል፤
- ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ተልዕኳቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን ይከታተላል፣ ለሚያቀርቡት ጥያቄ ተገቢው ምላሽ እንዲሰጣቸው ያደርጋል፣
- ከስራ ዘርፎች፣ ከተጠሪ ተቋማት እንዲሁም ከተለያዩ አካላት ለበላይ አመራሩ የሚላኩ ጉዳዮችን ምላሸ ይሰጣል፤ ውሳኔ የሚሹትን ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀርባል፤
- በፍትህ ሚኒስትር ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ከሕግና መ/ቤቱ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አንፃር በመለየት በማስረጃ ተደግፈው እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ ውሳኔ ሲያገኙ ተፈጻሚነታቸውም ክትትል ያደርጋል፣
- ለፍትህ ሚኒስትር መቅረብ ያለባቸው ጉዳዮች ቀጠሮ እንዲያዝላቸው ያደርጋል፣ጉዳዮችን በመለየት የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል ሲወሰንም ተፈጻሚነታቸውም ይከታተላል፣
- ለፍትህ ሚኒስትር እና ለጽ/ቤቱ የተመደበን በጀት ያስተዳድራል፣ ተለይቶ በሚሰጠው ዉክልና፣ ግዢ ወይም ክፍያ እንዲፈጸም ለሚመለከተው ጥያቄ ያቀርባል፣ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚያስፈልግ ግብአት መሟላቱን ያረጋግጣል፣
- በፍትህ ሚኒስትር የሚከናወኑ የጽሑፍ ግንኙነት፣ የስብሰባና የጉዞ ፕሮግራሞችን ይመራል፣
- የፍትህ ሚኒስትር የስብሰባ መርሃ ግብር እና ግዜ ሰሌዳዎች ያቀናጃል፣
- የፕሮቶኮል ሽፋን መሰጠት ለሚያስፈልጋቸው የበላይ አመራሮችና የውጭ እንግዶች መሰጠቱን ያረጋግጣል፣
- የበላይ አመራሩ የእንግዳ መስተንግዶ እና የሀገር ውስጥና የውጭ አገራት ጉዞ ዝግጅቶች አፈፃፀም ያመቻቻል፣ ይከታተላል፣
- ከዚህ በፊት የሕግ ኦዲት ቅሬታና ስነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት በደንብ ቁጥር 443/2011 አንቀጽ 91/2 ተሰጥቶ የነበረዉን የዲስፕሊን ጥፋት ሲፈፀም ለዋና ጉባኤ ወይም ለንኡስ ጉባኤዉ ክስ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
- የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ የሚገባቸዉን አመራሮችና ሰራተኞች ሃብታቸዉን ይመዘግባል፣ የምዝገባ ሰነዱን ለሚመለከተዉ መ/ቤት በወቅቱ መላኩን ይከታተላል፣
- ሀብታቸዉን ያስመዘገቡ አመራሮችና ሠራተኞች ወቅቱን ጠብቆ እድሳት እንዲያደርጉ ይከታተላል፣ ሲለቁ ክሊራንስ ከማግኘታቸዉ በፊት ዳግም ምዝገባ እንዲያካሂዱ ያከታተላል ፣ እሴቶችና የስነምግባር ደንቦች ማስረጽና ማስፈጸም የሚያስችሉ ስልቶች ይቀርፃል፣ መተግበሩን ይከታተላል፣
- ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጡ የስራ ክፍሎችንና ክፍተቶችን በጥናት በመለየት የመከላከያ ስትራቴጂ እንዲቀረፅ ያስተገብራል፣ ይታተላል፣
- ተቋማዊና የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ እንዲቀረፅ ያደርጋል፣
- ለተቋሙ ሰራተኞች የስነ-ምግባር ስልጠና እንዲሰጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፣