የዋናስራ አስፈጻሚ ተግባር እና ኃላፊነት

  1. በሥራ ክፍሉ ለተቋሙ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባር መሰረት ያደረገ ስራዎችን ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፤
  2. ለሥራ ክፍሉን የተመደበን በጀት ያስተዳድራል፤ 
  3. የሥራ ክፍሉን ንኡስ ማኔጅመንት ስብሰባዎች ይመራል፣ ውሳኔዎች መፈጸማቸውን ይከታተላል፤ 
  4. ለሥራ ክፍሉ የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤ 
  5. በስራ ክፍሉ የሚገኙ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ደረጃን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይገመገማል፤ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ ከግምገማውም በመነሳት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል፣ 
  6. ለሥራ ክፍሉ ተጠሪ ለሆኑ የስራ ክፍሎች ቅንጅታዊ አሰራርና ቋሚ የክትትልና ድጋፍ ስርአት ይዘረጋል፣ ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፤
  7. ለስራ ክፍሉ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና ጉዳዮች አስመልክቶ ውሳኔ ይሰጣል፣ በሕግ መሰረት በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ 
  8. የሥራ ክፍሉን ዕቅድ ለማሳካት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ይለያል፣ መፍትሔ እንዲያገኙም ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፤ 
  9. የሥራ ክፍሉን ተግባር እና ኃላፊነት በሚመለከት ከሚመለከታዉ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነዶች በመፈራምና የተለያዩ የግንኙነት አግባቦችና መድረኮች በማመቻቸት ሥራዉ ዉጤታማ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል፣ 
  10. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣ 
  11. በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ የስራ ክፍሎች የተለያዩ ግባዓቶች በማሟላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡