የመንግስት ሕግ እና ፍትህ አገልግሎት ሚ/ዴኤታ

የመንግስት ሕግ እና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን በዋናነት ቀደም ሲል በህግ ጉዳዮች አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ሲከናወኑ የነበሩ ተግባርና ኃላፊነቶች  እንደሚኖሩት ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ዘርፉ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል:- 

  1. ዘርፉን የሚመለከቱ ለፍትህ ሚኒስትር የተሰጡትን ስልጣንና ተግባር ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፤ 
  2. ለዘርፉ የተመደበን በጀት ያስተዳድራል፤ 
  3. የዘርፉን ንኡስ ማኔጅመንት ስብሰባዎች ይመራል፣ ውሳኔዎች መፈጸማቸውን ይከታተላል፤ 
  4. ለዘርፉና ከዘርፉ የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤ 
  5. በዘርፉ የሚገኙ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ደረጃን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይገመገማል፤ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ ከግምገማውም በመነሳት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል፣ 
  6. ለዘርፉ ተጠሪ ለሆኑ የስራ ክፍሎች ቅንጅታዊ አሰራርና ቋሚ የክትትልና ድጋፍ ስርአት ይዘረጋል፣ ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፤ 
  7. ለዘርፉ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና ጉዳዮች አስመልክቶ ውሳኔ ይሰጣል፣ በሕግ መሰረት በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈቱ ይመራል፣ 
  8. የዘርፉን ተልዕኮ ለማሳካት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ይለያል፣ መፍትሔ እንዲያገኙም ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፤ 
  9. ለፍትሕ ስርዓቱና ለተቋሙ ስትራተጅያዊ ዕቅድ፣ ለዘርፉ ተልዕኮ ስኬት ቁልፍ ድርሻ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ የህዝብ አደረጃጀቶችንና የግሉ ዘርፍ የሚሳተፉበት መድረክ እንዲካሄድ ያደርጋል፣ 
  10. የዘርፉን ተግባር እና ኃላፊነት በሚመለከት ከሚመለከታዉ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነዶች በመፈራምና የተለያዩ የግንኙነት አግባቦችና መድረኮች በማመቻቸት ሥራዉ ዉጤታማ የሚሆንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ 
  11. ለዘርፉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣ 
  12. ሌሎች ከፍትህ ሚኒስትሩ የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ 

የዘርፉ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት 

  1. ዘርፉን የሚመለከቱ ለፍትህ ሚኒስቴር የተሰጡት ስልጣንና ተግባር በማቀድ፣ ማደራጀት፣ በመምራትና በማስተባበር ይደግፋል፤ 
  2. ለጽ/ቤቱ የተመደቡ ዐቃብያነ ሕግ እና የአስተዳደር ሰራተኞች ያስተባብራል፣ ያሰማራል፣ የስራ አፈፃፀማቸው ይገመግማል፣ ይመዝናል፣ 
  3. የዘርፉን ንኡስ ማኔጅመንት ስብሰባዎች ያቀናጃል፣ ከዘርፉ ሀላፊ ጋር በመነጋገር ለማኔጅመንት ኮሚቴ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ለይቶ ያቀርባል፣ 
  4. የዘርፉ ኃላፊ ስትራቴጂያዊ አመራር እንዲሰጥ ለዘርፉ ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎች የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ያስተባብራል፣ 
  5. በዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ውሳኔዎችን አፈፃፀም ይከታተላል፣ 
  6. ለዘርፉና ከዘርፉ የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ተጠቃልለው እና ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ይከታተላል፤ 
  7. በዘርፉ የሚገኙ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ደረጃን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይገመገማል፤ግብረ መልስ ይሰጣል፣ 
  8. የዘርፉ ሀላፊ ለሚካፈሉባቸው ብሔራዊና አለም አቀፍ ስብሰባዎች አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች እና መግለጫዎች ተሟልተው መቅረባቸውን ያረግጣል፤ 
  9. በዘርፉ ተፈጻሚ የሚሆኑ ዝርዝር የአሰራር መመሪያዎች በማዘጋጀት ለዘርፍ ንኡስ ማኔጅመንት ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፡፡ 
  10. የዘርፉ ኃላፊ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በማይገኝበት ጊዜ ወክሎ ይሳተፋል፣ ለተለያዩ ስብሰባዎች እና ፕሮግራሞች የሚቀርቡ ንግግሮችን ያዘጋጃል፣ 
  11. ከዘርፉ ኃላፊ የሚመሩ እና ከተለያዩ አካላት ለሚቀርቡ ጉዳዮች ወይም ለዘርፉ ኃላፊ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ያስተናግዳል፣ ቅሬታው ሰንሰለቱን ጠብቆ መቅረቡን ያረጋግጣል፣ በሕግ መሰረት በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ በዘርፉ ኃላፊ ለሚወሰኑ ጉዳዮች አስተያየትና የውሳኔ ሓሳብ ያቀርባል፣ 
  12. ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ የሕግ ነክ የውሳኔ ሐሳቦች ምርምሮ ለዘርፉ ኃላፊ አስተያየት ያቀርባል፣ 
  13. የዘርፉን ሀላፊ የስብሰባ መርሃ ግብር እና የግዜ ሰሌዳዎች ያቀናጃል፣ በዘርፉ የሚከናወኑ የጽሑፍ ግንኙነት፣ የስብሰባና የጉዞ ፕሮግራሞችን አንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸው ስራዎችን ይመራል፣ 
  14. በዘርፉ ስር በተደራጁ የሥራ ክፍሎች መካከል ሊኖር ለሚገባውን ትስስርና መስተጋብር ስርዓት ይዘረጋል፣ ያቀናጃል፣ ይመራል፣ 
  15. ዘርፉን በሚመለከቱ ጉዳዮች በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል ፣ ለሚቀርቡ የድጋፍ ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ እንዲያገኙ ይከታተላል፣ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዲቀረፉ ያደርጋል፤ግብረ መልስ ይሰጣል፣ 
  16. ለዘርፉ ተልዕኮ ስኬት ቁልፍ ድርሻ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ የህዝብ አደረጃጀቶችንና የግሉ ዘርፍ የሚሳተፉበት መድረክ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ 
  17. ከዘርፉ ወጪ የሚሆኑ ደብዳቤዎችን፣ ሰርኩላሮችንና መመሪያዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መድረሳቸዉን ያረጋግጣል፣ 
  18. ለዘርፉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ጥያቄ ያቀርባል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣

Department Lead

በላይሁን ይርጋ

ሚኒስትር ዴኤታ