የሴቶችና የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የሴቶች እና ባለ ብዙ ዘርፍ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ሃላፊነት ይኖሩታል፡-

  1. ከብሄራዊ አስተባባሪ ጽ/ቤቱ የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነቶች ይፈጽማል፣ የብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴዉ ውሳኔዎች አፈፃፀም ይከታተላል፣ 
  2. ለብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴዉ የሴክሬትሪያት አገልግሎት ይሰጣል፣ 
  3. የብሄራዊ አስተባባሪ አባል ተቋማት ዕቅዶች ያቀናጃል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል የተጠቃለለ ሪፖርት ለሚመለከታቸው ያቀርባል፣ 
  4. የብሄራዊ አስተባባሪ አካሉን እስትራቴጂክ እቅድ ያዘጋጃል፣ እንደአስፈላጊነቱ እንዲከለስ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ 
  5. የፍትህና እንክብካቤ ማእከላት ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣ 
  6. የስራ ክፍሎች ሴቶችና ሕፃናትና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን በዕቅድ መካተቸዉን ያረጋግጣል፣ ዕቅድና አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ 
  7. በክልሎች የፍትህና እንክብካቤ ማእከላት እንዲደራጁ ድጋፍ ይሰጣል፣ 
  8. ሴቶች እና የባለብዙ ዘርፍ እና የስርአተ ጾታ ጉዳዩች የሚቀረፁ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ መመሪያዎች እና በዕቅዶች ተካተው እንዲፈፀሙ ስርዓት ይቀርፃል፣ መካተታቸውን ያረጋግጣል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  9. በሴቶች እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች አስመልክቶ የወጡ ህጐች እና አሠራሮች ዙሪያ የታዩ ክፍተቶች እና አዲስ በሚወጡት ህጐች ላይ አስተያየት ያቀርባል፣ የስርአተ ጾታ ኦዲት ያከናውናል፣ የኦዲት ግኝቱ ተግባራዊ መደረጉን ይከታተላል፣ 
  10. ለሴት ሰራተኞች የትምህርትና ስልጠና እድል እንዲመቻች ይሰራል፣ የሴት ሰራተኞች ፎረም እንዲጠናከር ድጋፍና ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ 
  11. ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዩች ዙሪያ ከሚሰሩ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፣ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኛ እና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካላት ምቹ መሆኑን ያረጋግጣል 
  12. ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች የሚመለከቱ በአላት ላይ አስተማሪ የሆኑ መድረኮችን ያዘጋጃል፣የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን የሚመለከቱ መረጃዎች ያደራጃል ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል፣ 
  13. ኤች.አይ.ቪ. በደማቸው የሚገኝ ሠራተኞችን ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮች መቀረፀቸውን ይከታተላል፣ 
  14. የሕፃናት ማቆያ በተቋሙ አስፈላጊ በሆኑ የስራ ቦታዎች መደራጀቱን እና አስፈላጊው ግብዓት መሟላቱን ያረጋግጣል፣ 
  15. በተቋሙ የሚገኙ ሰራተኞችን መረጃ በጾታ፣ በዕድሜ፣ የአካል ጉዳት ሁኔታ፣ በስራ ሃላፊነትና በትምህርት ደረጃ መረጃ ተለይቶ መያዙን ያረጋግጣል፣ 
  16. የአካባቢ ጥበቃና እና የተቋሙን ሰራተኞች ማህበራዊ ሀለፊነት ጉዳዮች በበላይነት ያቅዳል የስተባብራል፣ ተፈጻሚነታቸዉንም ያረጋግጣል፣ 
  17. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  18. ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ 
  19. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ 
  20. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  21. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤ 
  22. ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  23. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 
  24. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 
  25. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣ 
  26. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  27. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤ 

Department Lead

ዳግማዊት አላምኔ ትርፌ

ዳይሬክተር