የዘርፍ ስራ አስፈጻሚ ተግባር እና ኃላፊነት

የዘርፉ ስራ አስፈጻሚ በአዲስ መለክ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ውስጥ የተደራጀ ሲሆን በዘርፉ ከሚከናወኑት ተግባራት አንጻር በቅረበት የሚደግፍ የስራ ክፍል ማደራጀት በማስፈለጉ የተደራጀ የስራ ክፍል ነው፡፡ በስራ አስፈጻሚው ስር ሶስት ቡድኖች የተደራጁ ሲሆን የአስተዳደር ሰው ሀብት ልማት ቡድን፣ የግዥና ፋይናንስ ቡድን እና የዘርፉ የመዝገብ አያያዝ አስተዳደር ቡድን ይዞ የሚከተሉት ተግባር እና ኃላፊነት ይኖረዋል፡- 

  1. በሥራ ክፍሉ ለዘርፉ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባር መሰረት ያደረገ ስራዎችን ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፤
  2. የሥራ ክፍሉን የአስተዳደርና ፋይናንስ ስራዎችን ይመራል፣ ውሳኔዎች መፈጸማቸውን ይከታተላል፤ 
  3. በዘርፉ የሪከርድና ማህደር አያዝ በዘመናዊ የአሰራር ስርዓት እንዲታገዝና ለተገልጋዮች የተሸለ አገልግሎት መቅረቡን ይከታተላል፡፡ 
  4. ለሥራ ክፍሉ የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤ 
  5. በስራ ክፍሉ የሚገኙ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ደረጃን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይገመገማል፤ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ ከግምገማውም በመነሳት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል፣ 
  6. ለሥራ ክፍሉ ተጠሪ ለሆኑ የስራ ክፍሎች ቅንጅታዊ አሰራርና ቋሚ የክትትልና ድጋፍ ስርአት ይዘረጋል፣ ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፤
  7. ለስራ ክፍሉ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና ጉዳዮች አስመልክቶ ውሳኔ ይሰጣል፣ በሕግ መሰረት በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ 
  8. የሥራ ክፍሉን ዕቅድ ለማሳካት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ይለያል፣ መፍትሔ እንዲያገኙም ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፤ 
  9. በዘርፉ ውስጥ ለሚገኙ የስራ ክፍሎች የተለያዩ ግብዓቶች በማሟላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡