የመሰረታዊ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

የመሰረታዊ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ በአዲስ መልክ የተለያዩ የስራ ክፍሎች በማካተት የተደራጀ ነው፡፡ የስራ ክፍሉ ለተቋሙ ሥራ የሚያስፈልጉ የንብረት፣ የቢሮ አገልግሎት፣ የትራንስፖርት ሥምሪትና የተሽከርካሪ ጥገና፣ እንዲሁም የህንጻ አስተዳደርና ጥገና ሥራዎች አጠቃሎ የተደራጀ ሲሆን ዳይሬክቶሬቱ በስሩ የንብረት አስተዳደር ቡድን፣ የጠቅላላ አገልግሎት ቡድን፣ የህንጻ አስተዳደርና ጥገና ቡድን እና የትራንስፖርት ስምሪትና ጥገና ቡድን በመያዝ የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል:-

 1. በስራ ክፍሉ የሚሰጡ የንብረት አስተዳደርና የጠቅላላ አገልግሎቶችን ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣
 2. በተቋሙ ይዞታ ስር የሚገኙ ህንጻዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ እና ተስማሚ መሆናቸውን ይከታተላል፡፡
 3. በፌዴራል እና በክልል የሚገኙ የተቋሙ ህንጻችን አጠቃላይ መረጃ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ /profile/ በአግባቡ ተደራጅቶ መያዛቸውንና ወቅታዊ /update/ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
 4. በቢሮ አካባቢ የድንገተኛ አደጋ መከላከያ መሣሪያዎችና መገልገያዎች ተሟልተው መኖራቸውንና በትክክል መስራታቸውን ያረጋግጣል፣
 5. አዳዲስ የሥራ ዘርፎች በሚከፈቱበት ጊዜ የሚያስፈልጉ መሟላታቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
 6. ጥገና የሚፈልጉ የተቋሙ ህንፃዎች ቅድመ ጥናት ያደርጋል፣ መርሃ ግብር ያዘጋጃል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡ የጥገናና ዕድሳትት ሥራዉ የሥራ መዘርዝሩን ጠብቆ እየተፈፀመ መሆኑን ክትትል ያደርጋል፡፡
 7. ጥገና የሚፈልጉ የቢሮ መገልገያ እቃዎች (ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ የፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የውሃ፣ ኤሌትሪክ፣ የሽንት ቤት፣ ተሸከርካሪ ወዘተ. ከተጠቃሚ ክፍሎች የጥገና ጥያቄ ይቀበላል፣ ጥገና መደረጉን ይከታተላል፣
 8. የጥገናና ሌሎች የክፍያ ጥያቄዎች ሲቀርቡ አገልግሎት መሰጠቱን አጣርቶ ለሚመለከተዉ የሥራ ክፍል ያቀርባል፣
 9. በግዢና በስጦታ የተገኙ እቃዎችን አረጋግጦ ይረከባል፣ በንብረት መመዝገቢያ ሰነድ ላይ መዝግቦ ገቢ ያደርጋል፣ ለተጠቃሚዉ ክፍል መሰጠቱንና ለተገቢዉ አገልግሎት መዋሉን ይከታተላል፣
 10. የገቢና ወጪ ንብረት መረጃዎች በዘመናዊ መልኩ ተደራጀቶ እንዲያዝ ያደርጋል፣
 11. የተሸከርካሪዎች አጠቃላይ የህይወት ታሪክ መረጃ /profile/ በአግባቡ ተደራጅቶ መያዛቸውንና ወቅታዊ /update/ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
 12. የተሸከርካሪ አቅርቦት ከፍላጎት ጋር የሚጣጣምበት በፍትሃዊነት አገልግሎት የሚሰጥበትን አሰራር ይዘረጋል፣
 13. 13.የተቋሙ ተሽከርካሪዎች ተገቢዉ ጥገናና አመታዊ የቴክኒክ ምርመራ እንዲደረግላቸዉ ያደርጋል፣
 14. ለትራንስፖርት አገልግሎት የዋለው ነዳጅ ፍጆታ ከአቅራቢ ድርጅቶች መረጃ ተመሳከረ ሪፖርት ያሰባስባል፣ ክፍያ እንዲፈጸም ለሚመለከተዉ ያስተላልፋል፣
 15. ለተሽከርካሪ የሚያስፈልጉ አላቂ ዕቃዎችና መለዋወጫዎች በበቂ ሁኔታ እንዲገዙ ያደርጋል፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
 16. የትራንስፖርት ስምሪት የውስጥ አሠራር ይዘረጋል፣ ቅጾችን ወቅታዊ ያደርጋል፣ አተገባበሩን ይከታተላል
 17. የተሸከርካሪ ጉዳት የትራፊክ ሪፖርት እንዲቀርብ ያደርጋል፣ የመድን ዋስትና ጉዳይ ክትትል እንዲደረግና እንዲፈጸም ያደርጋል፣
 18. የቢሮ አገልግሎት ስራዎችን ማለትም የፎቶ ኮፒ፣ የጥበቃ፣ የጽዳት፣ የጉዳይ ማስፈጸም እና የመሳሰሉት ስራዎች በአግባቡ መሰጠቱን ይከታተላል፣
 19. በሕግ የደህንነት መጠበቂያና የደንብ ልብስ ለተፈቀደላቸው ሠራተኞች በወቅቱ የተሟላላቸዉ መሆኑን ይከታተላል፣ እየተጠቀሙበት መሆኑን ያረጋግጣል፣
 20. በጋራ የተያዙ ህንፃዎችን አስተዳደር፣እድሳት እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያ አፈፃፀም በሚመለከት ከፍርድ ቤት ጋር በጋራ ይሰራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
 21. በተቋሙ ምድረ-ግቢ ውስጥ ዉበትና ንፅህና ያስጠብቃል፣ ልዩ ልዩ አትክልቶች እንዲተከሉ ያደርጋል፣ በእንክብካቤ መያዛቸውን ይከታተላል፣
 22. በተቋሙ የተሸከርካሪ፣ የእቃዎች እና የባለጉዳይ የመግቢያና መዉጫ ፍተሻ እንዲሁም ባለጉዳዮች የያዙትን የጦር መሳሪያ መቀበያና መልሶ ማስረከቢያ ስርዓት ይዘረጋል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፣
 23. ገቢ የሚደረጉ ንብረቶች በመስፈርት መስረት መቅረባቸውን፣ በቢንካርድ እና ስቶክ ካርድ ላይ መስፈራቸውንና በተገቢው መንገድ መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፣
 24. የንብረት ወጪ መጠየቂያ ሰነዶችን ያፀድቃል፣ ወጪ የተደረጉ ንብረቶች በተገቢው መንገድ መዝገብ ላይ መስፈራቸውንና መወራረሳቸውን እንዲሁም ቋሚ እቃ ኮድ (ታግ) መሰጠቱን እና ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ያረጋግጣል፣
 25. የለቀቁ ሰራተኞች የተረከቡት የተቋሙን ንብረቶች ማስረከባቸውን አስፈላጊ ማጣራት ያደርጋል፤
 26. የተቋሙን ቋሚና አላቂ ንብረቶችን ቁጥጥርና ምዝገባ መካሄዱን ያረጋግጣል፣ ዓመታዊ የንብረት ቆጠራ እንዲካሄድ ያደርጋል፣ የቆጠራ ሪፖርት ያቀርባል፣
 27. የመጋዘኑን ንፅህናና ደህንነት መጠበቁን ይከታተላል፣ አላስፈላጊ የእቃዎች ክምችት እንዳይኖር ክትትል ያደርጋል፣ በስቶክ ያለውን ሚዛን በማየት የግዥ ጥያቄ ያቀርባል ወይም እንዲቀርብ ያደርጋል፣
 28. መወገድ የሚገባቸዉ ንብረቶች በመለየት እንዲወገዱ ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፣፣ የተወገዱት ከመረጃ ቋት እንዲሰረዙ ያደርጋል፣
 29. ለየስራ ክፍሎች በማዕከል አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ህትመት፣ የፎቶ ኮፒ፣ ጥረዛ እና ስካኒንግ አገልግሎት በዋና መ/ቤትና በሕግ ማስፈፀም ዘርፎች ዉስጥ ያደራጃል፣ አገልግሎት አሰጣጡን ይከታተላል፣
 30. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤
 31. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
 32. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
 33. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
 34. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
 35. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
 36. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
 37. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
 38. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
 39. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤

Department Lead

አቶ ብሩክ ጸጋዬ ፍቅሩ

ሥራ አስፈጻሚ