የግዥና ፋይናንስ የስራ ክፍል ቀደም ሲል በሁለት ዳሬክቶሬት ተከፍሎ በመስራት ላይ የሚገኙ የነበሩ ሲሆን በአዲሱ አደረጃጀት አንድ የስራ ክፍል ሆኖ የተደራጀ የሥራ ክፍል ሲሆን ተጠሪነቱ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኖ በስሩ የፋይናንስ ቡድንና የግዥ ቡድን ይዞ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል:-
- ከመንግሥት ግምጃ ቤትና ከለጋሽ ድርጅቶች የተገኘውን ገንዘብ ወደ መስሪያ ቤቱ የባንክ ሂሳብ ገቢ ያደርጋል፣
- ለተቋሙ የሚመደበውን በጀት በመንግሥት የፋይናንስ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና የአሠራር ሥርዓቶች ላይ በመመስረት አገልግሎቶችን ይሰጣል፣
- በተዘረጋዉ አሰራር መሰረት ለዘርፎቹና ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተመደበዉን ገንዘብ ለይቶ በተከፈተዉ የባንክ አካዉንት ገቢ ያደርጋል፣
- መረጃዎች የተሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ በሕግ መሰረት ክፍያዎችን ይፈፅማል፣ የሂሣብ ምዝገባ ያደርጋል፣
- የሂሳብ ሰነዶች በመለየት ይመዘግባል፣ በቅደም ተከተል እንዲደራጅ ያደርጋል፣ በአግባቡ ተጠብቀዉ መያዛቸዉን ይከታተላል፣
- የሂሳብ አያያዝ እና የክፍያ አፈጻጸም በደንብና መመሪያ መሠረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል ፣ ይከታተላል ፤
- ከመንግስት በየጊዜው የሚተላለፉ አዳዲስ የፋይናንስ መመሪያዎች ያስተዋውቃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
- በስራ ላይ ያሉ ልዩ ልዩ ቅጾችና ፎርማቶችን በትክክል በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል ፤
- የሠራተኞች የስራ ላይ መገኘትና የለቀቁ ሰራተኞች ሪፖርት ይሰበስባል፣ የለቀቁትን ለይቶ ከደመወዝ ክፍያ ሰነድ (ፔይሮል)እንዲወጡ ያደርጋል፣
- ያልተወራረዱ ክፍያዎችን ለይቶ ይከታተላል፣ እንዲወራረዱ ያደርጋል፣
- ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት በተቀመጠው አሰራር መሰረት ገቢ ይሰበስባል፣ በህጉ መሰረት ለመንግስት ገቢ ያደርጋል፣
- የተቋሙን የፋይናንስ አፈጻጸም መግለጫዎችና ሪፖርቶች በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ያቀርባል፣
- የመ/ቤቱን ሂሳብ በውስጥና በውጭ ኦዲተሮች ያስመረምራል፣ በኦዲት ሪፖርት ግኝት መሠረት የማስተካከያ እርምጃ መግለጫዎች ለኃላፊ ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
- ከሁሉም የሥራ ክፍሎች የአቅርቦት ፍላጎት መረጃ በማሰባሰብ የግዥ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
- የሚፈፀሙ ግዢዎች በመንግስት በወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት መሆኑን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
- ግዥ ከመፈጸሙ በፊት እቃዉ እስቶር መኖር አለመኖሩን መረጃ ይሰበስባል፣ በእስቶር የሚገኝ ከሆነ ለጠያቂዉ ክፍል ያሳዉቃል፣
- የገበያ ጥናት ያካሂዳል፣ የተፈላጊ እቃዎች ዋጋ፣ አቅርቦትና አቅራቢ ድርጅቶችን የተመለከቱ መረጃዎች ተሰብሰበዉ እንዲያዙ ያደርጋል፣
- ለሚገዙ ዕቃዎች ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ እና መጠን የያዘ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደረጋል፣
- የግዥ ዘዴ በመለየት የጨረታ ሰነድ ያዘጋጃል፣ ለተጫራቾች ማብራሪያ ይሰጣል፣ ጨረታ ይከፍታል፣ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
- የግዥ ውል ሂደት በሚገባ መካሄዱን ይቆጣጠራል፣ የዉል ስምምነቱን በአግባቡ የማይወጡት ላይ በህጉ መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
- በተሰጠው የገንዘብ ውክልና መጠን መሰረት ግዥ ያጸድቃል፣ ከአቅራቢዎች ጋር ውል ይገባል፣ ግዥም ይፈጽማል፣
- በማዕቀፍ የሚከናወኑ ግዢዉችን በመለየት ለሚመለከተዉ ተቋም በወቅቱ ይልካል፣ ግዢዉን ይከታተላል፣
- የጨረታ አሸናፊዉ እንደታወቀ ንብረቱ ገቢ እንዲሆን ለሚመለከተዉ የስራ ክፍል ያሳዉቃል፣ የተገዛውም ዕቃ ትክክለኛና በወጣው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ገቢ መሆኑን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
- የግዢ አፅዳቂ ኮሚቴ አስፈላጊዉን ግብዓት ያሟላል ለግዢዉ የተሟላ ሰነድና መረጃ በማቅረብ ድጋፍ ይሰጣል፣
- የግዥ ሰነዶችን በአግባቡ ይይዛል፣ ከሚመለከታቸው ሕጋዊ አካላት ማብራሪያ ሲጠየቅ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፣
- የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
- የተቋሙንና የሥራ ክፍሉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤
- ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
- የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
- በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
- ከዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
- ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
- የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
- በስራ ክፍሉ ተልእኮ ባለደርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
- የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤