የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት ተጠሪነቱ ለዋና ጉባኤ ሆኖ በስሩ የዐቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ቡድን ይዞ የተደራጀ ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል:- 

  1. የዐቃቤያን ሕግ ስምሪትና የአሰራር ዉጤታማነት ማሻሻያ ስርአት ይቀርፃል ይተገብራል፣
  2. ብቃት ያላቸዉ ዐቃቤያነ ሕግ ለመሳብና ያሉትን ለማቆየት የሚያስችል ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ክትትል ያደርጋል፣ 
  3. የዐቃቤያነ ሕግ የስራ የምዘና ሥርዓት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ይቀርፃል፣ በየወቅቱ እንደመዘኑ ይከታተላል፣ ዉጤቱን ከማህደርታቸው ጋር እናዲያያዝ ያደርጋል፣ 
  4. የዐቃቤያነ ሕግ የጾታና ብሄር ስብጥር እንዲጠና በማድረግ የማሻሻያ ዕቅድ ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ያስተገብራል፣ 
  5. ከጉባኤዉ ጋር በመሆን ለተቋሙ የሚያስፈልጉ ዐቃቤያነ ሕግ የስራ መደብ አይነት፣ ብዛትና ተፈላጊ ችሎታ ሰነድ ያዘጋጅል፣ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ክትትል ያደርጋል፣
  6. ከዘርፉ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጋር በመነጋጋር ክፍት የሥራ መደቦችን በመለየት እንደ አስፈላጊነቱ ዐቃቤያነ ሕግ በደረጃ ዕድገት፣ በቅጥር፣ በዝውውር እንዲሟሉ ያደርጋል፣
  7. የጉባኤው ውሳኔ በማይጠይቁ የዐቃቤያን ሕግ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፣ 
  8. ለዐቃቤያን ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባዔው የሴክሬታሪያት አገልግሎት ይሰጣል፣ በጉባኤው የተወሰኑ ውሳኔዎችን እና ቃለ-ጉባኤዎችን አደራጅቶ ይይዘል፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የፀደቁትን ውሳኔዎችን አፈፃፀም ይከታተላል፣ 
  9. በዐቃቤያን ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ ለሚዘጋጁ የተለያዩ መመሪያዎች ግብአት የማሰባሰብ ስራ ይሰራል፤ መነሻ የሚሆኑ ረቂቆችን ያዘጋጃል፤ 
  10. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አዲስ ለሚቀጠሩ ዐቃብያነ ሕግ የስራ የማስተዋወቂያ ስልጠና (Inducation) እንዲሁም ተግባር ተኮርና ሙያ ብቃት ማረጋጫ የቅድመ ስራ ስልጠና እንዲወስዱ ያደርጋል፣  
  11. ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን ለዐቃቤያነ ሕግ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ እንዱሁም የስራ ላይ ስልጠና እንዱያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ 
  12. የዐቃቤያን ሕግ ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ ለሠራተኞች ተስማሚና ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲፈጠር በሥራ አካባቢ የሚኖሩ ችግሮችን በመዳሰስ የመፍትሔ እርምጃ በማቅረብና በማስወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፤ 
  13. በግልፅ ተለይቶ በተሰጠዉ ዉክልና መሰረት የዐቃቤያን ሕግን የሚመለከቱ ዉሎች ይዋዋላል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ 
  14. የዐቃቤያነ ሕግ የስራ ላይ መገኘት ሪፖርት ይሰበስባል፣ በስራ ላይ ያሉና የለቀቁትን ለይቶ በወቅቱ ለሚመለከተዉ የስራ ክፍል በፅሁፍ ያሳዉቃል፣ 
  15. ለዐቃብያነ ሕግ በመንግስት የተሠጡ ቤቶችን አስመለክቶ መረጃ አደራጅቶ ይይዛል፣ ሲለቁ ለተቋሙ መመለሳቸዉን ያረጋግጣል፣ 
  16. የዐቃብያነ ሕግን የግል ማህደር አደራጅቶ ይይዛል፣ የመረጃ ቋት ያደራጃል፣የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ያዘምናል፣ ያስተዳድራል፣ 
  17. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤ 
  18. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣  
  19. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ 
  20. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
  21. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤ 
  22. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
  23. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
  24. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
  25. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣ 
  26. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ 
  27. በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤

Department Lead

ጌታነህ ሀብታሙ ገለታ

ዳይሬክተር