የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሃብት አስተዳደር ዳይሬክተር ተጠሪነቱ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

  1. ዘርፉን የሚመለከቱ ለፍትህ ሚኒስቴር የተሰጡትን ስልጣንና ተግባር ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፤
  2. ለዘርፉ የተመደበን በጀት ያስተዳድራል፤
  3. የዘርፉን ንኡስ ማኔጅመንት ስብሰባዎች ይመራል፣ ውሳኔዎች መፈጸማቸውን ይከታተላል፤
  4. ለዘርፉና ከዘርፉ የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ያረጋግጣል፤ 
  5. በዘርፉ የሚገኙ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ደረጃን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይገመገማል፤ግብረ መልስ ይሰጣል፣ ከግምገማውም በመነሳት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል፣ 
  6. ለዘርፉ ተጠሪ ለሆኑ የስራ ክፍሎች ቅንጅታዊ አሰራርና ቋሚ የክትትልና ድጋፍ ስርአት ይዘረጋል፣ ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፤ 
  7. ለዘርፉ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና ጉዳዮች አስመልክቶ ውሳኔ ይሰጣል፣ በሕግ መሰረት በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ 
  8. የዘርፉን ተልዕኮ ለማሳካት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ይለያል፣ መፍትሔ እንዲያገኙም ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፤
  9. ለፍትሕ ስርዓቱና ለተቋሙ ስትራተጅያዊ ዕቅድ፣ ለዘርፉ ተልዕኮ ስኬት ቁልፍ ድርሻ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ የህዝብ አደረጃጀቶችንና የግሉ ዘርፍ የሚሳተፉበት መድረክ እንዲካሄድ ያደርጋል፣
  10. የዘርፉን ተግባር እና ኃላፊነት በሚመለከት ከሚመለከታዉ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነዶች በመፈራምና የተለያዩ የግንኙነት አግባቦችና መድረኮች በማመቻቸት ሥራዉ ዉጤታማ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል፣
  11. ለዘርፉ የሚያስፈልገው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣
  12. ሌሎች ከሚኒስትር የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

Department Lead

አቶ ኖህ ታከለ ወልደሀዋሪያት

ዳይሬክተር