የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክልል ጉዳዮች ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ሆኖ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ተግባር እና ኃላፊነቶችን የሚፈጽም ይሆናል፡-
- የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤
- ከስራ ክፍሉ ጋር ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች ለመቅረጽ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
- የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
- በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
- ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
- ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
- ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
- የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
- በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
- የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤
- በውክልና የተሰጡ ጉዳዮችን ክትትል የሚደረግበትን ስርዓት ይዘረጋል፣ ክትትል ያደርጋል ድጋፍ ይሰጣል፣
- በውክልና የተሰጡ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለሚነሱ የሕግ እና ሌሎች ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፣
- ከክልል በውክልና የተሰጡ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ እና የሰበር የሚታዩ ጉዳዮችን ይከታተላል፣
- በውክልና ለተሰጡ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ በጀት ድጎማ ቀመር እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በጀት ጥያቄያቸው የተመለሰ መሆኑን ያረጋግጣል፣
- በውክልና የተሰጡ ጉዳዮችን አፈጻጸም ውጤታማነት ለማረጋገጥ የስልጠና ፍላጎት ይለያል፣ ያደራጃል፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ ስልጠና ይሰጣል፣
- በክልል በውክልና የሚታዩ የፌዴራል ጉዳዮች የሚሰጡ የዐቃቤ ሕግ ውሳኔዎች ላይ ከሕግ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን የሕግ እና የውሳኔ ኦዲት ኢንስፔክሽን ያከናውናል፣ በግኝቶቹ መሰረት አስፈላጊው ማስተካከያ እንዲወሰድ ለወንጀል ጉዳዩ ዘርፍ እና ለክልሉ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ የውሳኔ ሀሳቡ ተቀባይት ሲያገኝ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
- በውክልና በተሰጡ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ያስተናግዳል፣ ምላሽ ይሰጣል፣
- የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ያመቻቻል፣ በክልል እና በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋማት ያሉ ምርጥ ተሞክሮ ማካፈያ መድረክ ያመቻቻል፣
- ተቀራራቢ የዐቃቤ ሕግ ውሳኔ እንዲኖር የጋራ አሰራር ይቀርጻል መተግበሩን ይከታተላል
- በተጨማሪም ከዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ተግበራትን ያከናውናል።