የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተግባር እና ኃላፊነት

የዘርፍ ጽ/ቤት ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ድጋፍ የሚሰጥ የስራ ክፍል ነው፡፡ ጽ/ቤቱም በስሩ የቅሬታ መቀበያና ማስተናገጃ ቡድን ይዞ፣ የአስተዳደር እና ፋይናንስ ማስተባበሪያ እና የዘርፉ የመዝገብ አያያዝ አስተዳደር ቡድን ሲሆኑ የሚከተሉት ተግባር እና ኃላፊነት ይኖረዋል፡- 

  1. ዘርፉን የሚመለከቱ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋም የተሰጡትን ስልጣንና ተግባር በማቀድ፣ በማደራጀት፣ በመምራትና በማስተባበር ይደግፋል፤ 
  2. ለጽ/ቤቱ የተመደቡ ዐቃብያነ ሕግ እና የአስተዳደር ሰራተኞች ስራ ያስተባብራል፣ ያሰማራል፣ የስራ አፈፃፀማቸው ይገመግማል፣ ይመዝናል፣ 
  3. የዘርፉን ንኡስ ማኔጅመንት ስብሰባዎች ያቀናጃል፣ ከዘርፉ ሀላፊ ጋር በመነጋገር ለማኔጅመንት ኮሚቴ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ለይቶ ያቀርባል፣ 
  4. የዘርፉ ኃላፊ ስትራቴጂያዊ አመራር እንዲሰጥ ለዘርፉ ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎች የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ያስተባብራል፣ 
  5. በዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ውሳኔዎችን አፈፃፀም ይከታተላል፣ 
  6. ለዘርፉና ከዘርፉ የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ተጠቃልለው እና ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ይከታተላል፤ 
  7. በዘርፉ የሚገኙ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ደረጃን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይገመገማል፤ግብረ መልስ ይሰጣል፣ 
  8. የዘርፉ ሀላፊ ለሚካፈሉባቸው ብሔራዊና አለም አቀፍ ስብሰባዎች አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች እና መግለጫዎች ተሟልተው መቅረባቸውን ያረግጣል፤ 
  9. በዘርፉ ተፈጻሚ የሚሆኑ ዝርዝር የአሰራር መመሪያዎች በማዘጋጀት ለንኡስ ማኔጅመንት ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ 
  10. የዘርፉ ኃላፊ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በማይገኝበት ጊዜ ወክሎ ይሳተፋል፣ ለተለያዩ ስብሰባዎች እና ፕሮግራሞች የሚቀርቡ ንግግሮችን ያዘጋጃል፣ 
  11. ከዘርፉ ኃላፊ የሚመሩ እና ከተለያዩ አካላት ለሚቀርቡ ጉዳዮች እና ቅሬታዎችን ያስተናግዳል፣ ቅሬታው ሰንሰለቱን ጠብቆ መቅረቡን ያረጋግጣል፣ በሕግ መሰረት በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ በዘርፉ ኃላፊ ለሚወሰኑ ጉዳዮች አስተያየትና የውሳኔ ሓሳብ ያቀርባል፣ 
  12. ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ የውሳኔ ሐሳቦች ምርምሮ ለዘርፉ ኃላፊ አስተያየት ያቀርባል፣ 
  13. የዘርፉን ሀላፊ የስብሰባ መርሃ ግብር እና የግዜ ሰሌዳዎች ያቀናጃል፣ በዘርፉ የሚከናወኑ የጽሑፍ ግንኙነት፣ የስብሰባና የጉዞ ፕሮግራሞችን አንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸው ስራዎችን ይመራል፣ 
  14. በዘርፉ ስር በተደራጁ የሥራ ክፍሎች መካከል ሊኖር ለሚገባውን ትስስርና መስተጋብር ስርዓት ይዘረጋል፣ ያቀናጃል፣ ይመራል፣ 
  15. ለአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል ፣ ለሚቀርቡ የድጋፍ ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ እንዲያገኙ ይከታተላል፣ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዲቀረፉ ያደርጋል፤ግብረ መልስ ይሰጣል፣ 
  16. ለዘርፉ ተልዕኮ ስኬት ቁልፍ ድርሻ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ የህዝብ አደረጃጀቶችንና የግሉ ዘርፍ የሚሳተፉበት መድረክ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ 
  17. ከዘርፉ ወጪ የሚሆኑ ደብዳቤዎችን፣ ሰርኩላሮችንና መመሪያዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መድረሳቸዉን ያረጋግጣል፣ 
  18. ለዘርፉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ጥያቄ ያቀርባል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ 
  19. ከባለድርሻ አካላት (ገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የንግድ አሰራር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን፣ ከፌዴራል ስምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን፣ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና ከመሳሰሉት) ጋር ያለውን የቅንጅታዊ አሰራር ሁኔታ ያስተባብራል፣ 
  20. በዐቃብያነ ሕግ እና የስራ ክፍሎች በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ያስተናግዳል፣ ቅሬታው ሰንሰለቱን ጠብቆ መቅረቡን ያረጋግጣል፣ 
  21. ዘርፉ የጠቅላላ አገልግሎት (የቢሮ አገልግሎት፣ የተሸከርካሪ ስምሪት እና ጥገና፣ የፎቶ ኮፒ፣ ስካኒንግ አገልግሎት፣ የመሳሰሉት) ማግኘቱን ያረጋግጣል፣ 
  22. የምስክሮች አበል ክፍያን በህጉ መሰረት መፈጸሙን ይከታተላል፣ 
  23. በዘርፉ የሚገኙ ሰራተኞች ወርሀዊ የስራ ላይ መገኘት ሪፖርት ከየስራ ክፍሎች በማረጋገጥ አጠቃሎ ለሚመለከተው አካል ይልካል፣ 
  24. ተንቀሳቃሽ እና ውሳኔ ያገኙ የችሎት እና የአስተዳደር መዝገቦችን ያደራጃል፣ ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል 
  25. ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ሚስጥራዊ ሪከርዶችና ሰነዶች የመለያ ኮድ እንዲዘጋጅላቸውና ተገቢውን ጥበቃ ክትትል ያደርጋል፣ 
  26. በመዝገብ አያያዝ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከተገልጋዮች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል ምላሽ ይሰጣል፣ 
  27. ውሳኔ ያገኙ (የማይንቀሳቀሱ መዛግብትን) መዛግቶብች በአግባቡ ተደራጅተው መቀመጣቸውን እና መጠበቃቸውን ይከታተላል፣ 

Department Lead

በረከት ማሞ ኤልታሞ

የጽ/ቤት ሃላፊ