ዜና

ኢትዮጲያ እና አሜሪካ ግንኙታቸውን ስለሚያጠናክሩበት ሁኔታ ተወያዩ

ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግስት ህግ እና ፍትህ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ከ JOHN ” JT ” TOMASZEWSKI (Africa policy Ranking member JiM Risch (R-ID) U.S. Senate Committee on foreign Relations) ጋር ኢትዮጲያ እና አሜሪካ በጋራ ትብብር ስለሚያደረጉባቸው ጉዳዮች እና በሽግግር ፍትህ ዙሪያ  በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል

በውይይታቸውም ሁለቱ ሃገራት በጋራ ትብብር ስላከናወኗቸው ተግባራት እና  የታቀዱ ስራዎችን በትብብር ከመስራት አንፃር እንዲሁም ግንኙነታቸውን በበለጠ ማጠናከር ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች የተወያዩ ሲሆን ሚንስትር ዴኤታው የሽግግር ፍትህ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ አብራርተውላቸዋል፡፡

በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጲያ ዲያስፖራዎችን ጥያቄ በሽግግር ፍትህ የሚታይበትን አግባብ በተመለከተም የተወያዩ ሲሆን በቀጣይ በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች እና ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረው  ለቀጣይ ስራዎችም አቅጣጫ አስቀምተዋል፡፡